በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ኢንተርናሽናል ጨዋታዎች እንዲሁም በሌሎች ምክንያቶች የተራዘሙት የኢትዮጵያ ፕሪመርሊግ ጨዋታዎች ዋናውን መርሃ ግብር ባላስተጓገለ መልኩ የሚያስኬድ ፕሮግራም ማውጣቱን ፌዴሬሽኑ ዛሬ ለሚድያዎች በላከው ደብዳቤ አስታውቋል።
በሁለተኛው እና ሥስተኛው ሳምንት መካሄድ የነበረባቸው ከታች የተዘረዘሩት ስድስት ጨዋታዎች ታህሳስ 18 ና 19 2011 ሚካሄዱ ይሆናል።
ቀን የተቆረጠላቸው ተስተካካይ መርሐ ግብሮች የሚከተሉትን ይመስላሉ
ረቡዕ ታኅሳስ 17 ቀን 2011
- ማሰታውቂያ -
09:00 ድሬዳዋ ከተማ ከ ደቡብ ፖሊስ (ሐረር)
09:00 ባህር ዳር ከተማ ከ ስሑል ሽረ (ባህር ዳር)
09:00 መቐለ 70 እ. ከ ፋሲል ከነማ (መቐለ)
11:00 ኢትዮጵያ ቡና ከ ወልዋሎ ዓ/ዩ (አአ)
ሐሙስ ታኅሳስ 18 ቀን 2011
09:00 ወላይታ ድቻ ከ ሲዳማ ቡና (ሶዶ)
11:00 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ጅማ አባ ጅፋር (አአ)
የተስተካካይ ጨዋታዎቹ ረቡዕ እና ሐሙስ ከተደረጉ በኋላ የስምንተኛ ሳምንት መደበኛ ጨዋታዎች ቅዳሜ እና እሁድ እንደሚቀጥሉ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።