በኢትዮዽያ ከፍተኛ ሊግ በምድብ-ሀ 29ኛው ሳምንት ተስተካካይ የምድቡን ጨዋታ በአዲስአበባ እስታዲየም ያደረጉት ሱሉልታ ከተማ ከ ለ መቐለ ከተማ ጨዋታ በሁለተኛው አጋማሽ መቐለ ከተማ 1-0 በሆነ ውጤት በመመራት አየቀጠለ በነበረበት ሰዓት በ66ኛ ደቂቃ አርቢተር ደረጄ ገብሬ አወዛጋቢውን ፍፁም ቅጣት ምት ለመቐለ ከተማ በመስጠታቸው የሱሉልታ ከተማ ተጫዋቾች የፍፁም ቅጣት ምቱን በመቃወም እንዲሁም በደጋፊዎቻቸው ጫና ከሜዳ ለቀው ሊወጡ ችለዋል፡፡
ኢትዮዽያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በትላንትናው እለት አመሻሹን ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ለጨዋታው መቋረጥ ጥፋተኛ ናቸው በሚል የዕለቱን ዋና ፌዴራል ዳኛ ደረጄ ገብሬ ላይ ለአንድ ዓመት ከማንኛውም የጨዋታ ወድድሮች እንዳያጫውቱ ቀጣቱን አስተላልፏል፡፡