የኢትዮጵያና ሩዋንዳ ጨዋታ የቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጭት ሽፋን ያገኛል
ለ2020 ቻን ማጣሪያ መስከረም 11 በትግራይ ስታድየም ሚካሄደው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እና የሩዋንዳ አቻው ጨዋታ በትግራይ ቴሌቪዥን የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ሚያገኝ ይሆናል።
በትግራይ ስታድየም ሚካሄዱ ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደ ተመልካቾቹ ሚያደርሰው ትግራይ ቲቪ ዋልያዎቹ ለመጀመርያ ጊዜ በትግራይ ስታድየም ሚያካሂደውን ጨዋታ በቀጥታ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንደሚያደርስ አስታውቋል።
በመቐለ ዝግጅቱን እያደረገ ሚገኘው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ትላንት ከንአን ማርክነህ እና ጀማል ጣሰው ካጋጠማቸው መጠነኛ ጉዳት ውጪ ሙሉ ስብስቡ በሙሉ ጤንነት ይገኛል።