የኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻውን አነጋጋሪ ቃለ-ምልልስ በነገው ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ላይ ይጠብቁ፤ ሀትሪክ በሀገር ውስጥ የስፖርት ዘገባዋ ነገ ለንባብ ስትበቃ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ባተረፈላት THE BIG INTERVIEW አምዷ የሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ
ኤክስኪዩቲቭ ኤዲተር እና ጋዜጠኛ የሆነው
ይስሀቅ በላይ በኢንስትራክተሩ መኖሪያ
ቤት ተገኝቶ ላደረገው ድፍረት የተሞላበት ጥያቄ ኢንስትራክተሩ ድፍረት የተሞላበትን ምላሽ ሰጥተዋል፤ ግን ምን ብለው ይሆን? በተወዳጇ እና በተናፋቂዋ ጋዜጣ ምላሻቸውን ያገኙታል፤ ለኢንስትራክተሩ ቀርበው በነበሩት ጥያቄዎች ከሰጡት ምላሽ ውስጥ በጥቂቱ የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡
“በእኔ ላይ ስም ማጥፋት ላይ የተሰማሩትን በህግ ለመፋረድ
የፍ/ቤት መከፈትን እየጠበኩ ነው” ሲሉ በፕሮጀክታቸው እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዙሪያም ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ከዚህ በታች ያለውን ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
“ብ/ቡድኑ ጅቡቲና ቻይና ተወውና መንግስተ ሰማያትም ቢሄድ አብሬ እንደምሄድ
አንተም ወሬውን የሚያናፍሱትም እንድታውቁት እፈልጋለሁ” ያሉበት ሲጠቀስ ሌላኛው ደግሞ
“ስልጣኔን ተጠቅሜ አንድም ተጫዋች አልመረጥኩም፤ መራጩ
እኔ ብሆን ደግሞ ሃያ ሁለቱንም ከእኔ ፕሮጀክት እመርጥ ነበር”የሚል ይገኝበታል፡፡
የነገዋ ሀትሪክ አታምልጦት፤ ሀትሪክ በሌላ የሀገር ውስጥ ዘገባዋ ዋልያዎቹ በመቐለ ኢንተርናሽናል ስታድየም የፊታችን እሁድ ከሩዋንዳ አቻቸው ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ዙሪያ የቡድኑ ተጨዋች አማኑኤል ዮሃንስ የሚሰጠው መልስ ይቀርብሎታል፤ ከዛ ውጪም ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ከተጨዋቾች ደመወዝ ጋር በተያያዘ
የፌዴሬሽኑን ውሳኔ ስለተቃወመበት ውሳኔ መረጃን እንሰጦታለን፡፡
ሀትሪክ በባህር ማዶ ዘገባዋም የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የሳምንቱ መጨረሻ የውስጥ ውድድርን እና ስለሌሎችም አስገራሚ የሆኑና ሊያነቡት የሚችሉትን እግር ኳሳዊ የስፖርት መረጃዎችን ታቀርቦሎታለች፡፡
ሀትሪክ የእርስዎ ናት፡፡
የሀትሪክ ስፖርት የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል