በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ወላይታ ድቻ ትናንት እና ዛሬ ሲመክር ውሎ በክለቡ አሰልጣኝ እና አመራሮች ላይ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል። በዚህም መሰረት የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ አሰፋ ሆሲሶ፣ ቴክኒካል ዳይሬክተሩ ታደሰ መታፈሪያና የደጋፊዎች ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ አንዷለም ከሀላፊነታቸው ተነስተዋል፡፡
የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ አሰፋ ሆሲሶ
የወላይታ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የወላይታ ድቻ ፕሬዝደንት አቶ ጎበዜ እንደገለጹት “አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ ከክለቡ ጋር ውል ስላላቸው ወደ ስራቸው እንዲመለሱ ደብዳቤ ወጥቷል።” የክለቡ ፕሬዝዳንት አክለውም “የቦርዱ ውሳኔ በነገው መድረክም ይቀጥላል።” ብለዋል። በነገው እለት የሚኖሩትን ውሳኔዎች በትኩሱ የምናደርሳችሁ ይሆናል።
- ማሰታውቂያ -
አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ
ወላይታ ድቻ በዘንድሮው የሊጉ ጉዞ ካደረጋቸው 8ጨዋታዎች በ1 ብቻ በማሸነፍ በ3 አቻ ተለያይቶ በ4ቱ ተሸንፎ ማግኘት ከሚገባው 24ነጥቦች 6ቱን ብቻ በማሳካት የሊጉ ግርጌ ላይ ተቀምጧል።