ወልዋሎ አዲግራት ዮንቨርሲቲ ከ መቐለ ከተማ ጋር የሚያደረገው ተስተካካይ መርሐ ግብር ጨዋታ አዲስአበባ ስታዲየም ላይ እንደማይከናወን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።
ወልዋሎ አዲግራት ዮንቨርሲቲ ከ መቐለ ከተማ ጋር የሚያደርጉት የተስተካካይ መርሐ ግብር ጨዋታ በአዲስአበባ ስታዲየም የፊታችን አርብ ግንቦት 17 ቀን 2010 እንዲደረግ የኢትዮጵያ እግርኳስ መወሰኑ እሚታወስ ሲሆን ፣ ወልዋሎ አዲግራት ዮንቨርሲቲ በአንፃሩ ጨዋታው አዲስአበባ ስታዲየም መደረግ ያለበትም በሚል ለፌዴሬሽኑ የቅሬታ ደብዳቤ ማስገባቱ ሲታወቅ ፣ በተጨማሪ
የትግራይ ክልል ኮማንድ ፖስት ለኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጨዋታውን ለማካሄድ በቂ የፖሊስ ሀይል እንዳለው በላከው ደብዳቤ መግለፁን አስመልክቶ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጨዋታውን በመጪው ግንቦት 17 ቀን 2010 በ9:00 ሰዓት በሸሬ ሜዳ እንዲካሄድ ውሳኔ ማሳለፉ ታውቋል።