የጅማ አባጅፋር እግር ኳስ ክለብ ለደጋፊዎቹ በቂ መረጃ ለመስጠት እንዲሁም ድጋፍ ማድረግ የሚያስችል አጭር የፅሁፍ መላኪያ መስመር ይፋ አደረገ።
የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ እስከዳር ዳምጤ በሰጡት መግለጫ ክለቡ ለደጋፊዎቹ በቂ መረጃ ለመስጠት እንዲሁም ድጋፍ እንዲያደርጉለት አዲስ አሰራር ዘርግቷል።
በመሆኑም ደጋፊዎች ለክለቡ አባልነት ለመመዝገብ በነፃ 6732 help ብለው በሞባይላቸው አጭር የፅሁፍ መልክት እንዲልኩ በማድረግ መመዝገብ ይችላሉ።
ይህን ካደረጉ በኋላ በሳምንት አንድ ብር ብቻ እየተቆረጠባቸው አጠቃላይ ክለቡን በተመለከተ ያሉ የዝውውር መረጃዎች ፣ የክለቡን ደረጃና የጨዋታ ውጤት መረጃዎችን የሚያገኙ ይሆናል።
በዚሁ አሰራር ደጋፊዎች በወር፣ በግማሽ ዓመትና በዓመት ጥሩ የሚሉቱን የክለቡን ተጫዋችም መምረጥ የሚችሉም ይሆናል ።
- ማሰታውቂያ -
መተግቢያውን የሰሩት የናናሰርቪስስ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ አብርሃም ደጉ በበኩላቸው አሰራሩ በክለቡና በደጋፊዎች መካከል ፈጣንና የተቀላጠፈ ግንኙነት ይፈጥራል ብለዋል።
አሰራሩ የደጋፊዎችን የአባልነት ምዝገባና ክለቡ በተመለከተ መረጃ ከመስጠት ባለፈ ሌሎች አገልግሎቶች እንደሚኖሩትም ጠቁመዋል።
ከነዚህም መካከል ደጋፊዎች የክለባቸውን ማልያ ለመግዛት እንዲሁም የክለቡን ጨዋታ ለመታደም የትኬት ግዥ የሚፈፅሙበት ለማድረግ ታስቧል ብለዋል።