ወደ ኘሪሜየር ሊጉ ለመግባት መቐለ ከተማ እና ሀዲያ ሆሳዕና ዛሬ በ10 ሰዓት በድሬዳዋ እስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ከ1-0 ከመመራት ተነስተው መቐለ ከተማ 2-1 አሸንፈው የ2010 የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ ተሳተፎቸውን ያረጋገጡበት ጣፋጭ ድል አስመዝግበዋል፡፡
ከጨዋታው መጀመረ ቀደም ብለው የሁለቱ ክለብ ደጋፊዎቹ በከተማው የተለየ ድምቀትን ፈጥረው ተያተዋል፡፡
ልክ 10:02 ሲል ጨዋታውን በክብር እንግድነት ያስጀመሩት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሊግ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አበበ ገላጋይ እና የድሬዳዋ እግርኳስ ፌዴሬሽን እና የክብር እንግዶች በመገኘት ከየቡድኖቹ ጋር ሰላምታ ተለዋውጠዋል ።
ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት የመሩት ኢንተርናሽናል አርቢትር ባምላክ ተሰማ አስጀምረዋል፡፡
- ማሰታውቂያ -
የጨዋታው የመጀመሪያው ደቂቃዎች ሁለቱም ቡድኖች ወደ ጎል የመድረስ እንቅስቀሴን አሰይተዋል፡፡
በ9ደቂቃ በእሰታዲየም ውስጥ ንፋስ የቀላቀለ ሀይለኛ ዝናብ በመጣሉ የመሀል ዳኛው ባምላክ ተሰማ ጨዋታውን ለማቋረጥ ተገደዋል፡፡
በስታዲየሙ በተለምዶ አጠራር ካታንጋ ግራና ቀኝ የጠቀመጡት ብዙ ሺ ኪሎሜተር አቆራርጠው የመጡ የሀዲያ ና መቐለ ከተማ ደጋፊዎች ዝናቡ ሳይበግራቸው ቡድናቸውን ሲያበረታቱ ተስተውሏል፡፡
ለ10ደቂቃዎች ተቋርጦ የነበረው ጨዋታ ዝናቡ በማበራቱ የእለቱ አርቢተሮች ሜዳው ማጫውት እንደሚችል ለማረጋገጥ ወደሜዳ በመግባት በሁለቱም የግብ ጠባቂ ቦታዎች አሸዋ እንዲደፋ በማድረግ ጨዋታውን አስጀምረዋል፡፡
ጨዋታው እንደተጀመረ ተደጋጋሚ ወደ ጎል መድረስ የቻሉት ሀዲያዎች ሲሆኑ በ14ኛው ደቂቃ ላይ እንዳለ ደባልቄ ሀዲያን ቀዳሚ ማድረግ ቻሏል፡፡
ሀዲያ ሆሳዕናዎች በመሪነት መዝለቅ የቻሉት ለ2ደቂቃዎች ነበር በ16ኛ ደቂቃ ላይ መቐለ ከተማ አቻ እሚያደርጋቸውን ድንቅ ጎል አማኑኤል ገብረሚካኤል ከርቅት በግምት ከ30ሜትር ላይ አስቆጥር አቻ ማድረግ ችሏል፡፡
በሁለተኛው አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች የተመጣጠነ ወደ ጎል የመድረስ ሙከራ ሲያደረጉ ተስተውሏል፡፡
በ76ኛ ደቂቃ ላይ በተገኘ የቅጣት ምት በቀጥታ በመታት መቐለ ከተማን ወደ ኘሪሜየር ሊጉ የገባበትን የመሸነፊያ ድንቅ ጎል ዮሴፍ ሀይሌ አስቆጥሯል፡፡
የመጨረሻ ደቂቃዎች ሀዲያ ሆሳዕና ተጭነው፡ጎል ለማስቆጠር ተንቀሳቅሰዋል ሆኖም ግብ ማስቆጠር ሳይችሉ ጨዋታው በመቀለ ከተማ 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
የአሰልጣኞች አስተያየት
ጌታቸው ዳዊት (መቀለ ከተማ)
ጨዋታው ለሁለታችንም ወሳኝ ነበረ ሆኖም በታክቲክ ረገድ የተሻልን ነበር ሀዲያዎች ጉልበትን ተመስርተው ነበር የተጫወቱት እኛ ግን በማይድ ጌም በልጠናቸዋል፡፡ ያገኘናቸውን የጎል አጋጣሚዎች በሚገባ ተጠቅመን አሸንፈን ወጠናል፡፡
ጳውሎስ ጌታቸው (ሀዲያ ሆሳዕና)
ሙሉ ዝግጅት አድረገን ነው የመጣነው ሆኖም ዛሬ የኛ ቀን፡አልነበረም የቀንም ጀግና አለው፡፡ ልጆቼ የቻሉት አድርገዋል ሁለት በሰራናቸው ስህተቶች ተሸንፈን ወጠናል፡፡ የሀዲያ ደጋፊዎች በጣም ላመሰግናቸው እወደለሁ፡፡ የነበርንበት ምድብ ከባድ ነበር ሆኖም በሄድንበት እየሄዱ ደግፈውናል እሚፈልጉት ነገር፡ባለመሣካቱ በጣም አዝኛለሁ ፤ እነዚህን ደጋፊዎች ከኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ጋር ለይቼ አላያቸውም፡ አንድ ቀን እክሳቸዋለሁ፡፡