በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውና የፊታችን ቅዳሜ በአፋርዋ ሰመራ ከተማ እንደሚካሄድ ቀጠሮ የተያዘለት የፕሬዘዳንትና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫ በተያዘለት ቀን መካሄዱ አጠራጣሪ ሆናል።
ታማኝ የዜና ምንጮች በተለይ ለሀትሪክ ድህረ- ገጽ እንደገለፁት ፊፋ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽና ለአስመራጭ ኮሚቴው በላከው ጠንከር ያለ ደብዳቤ መስረት የምርጫው ሂደት በችግሮች የተሞላ በመሆኑና የተለያዩ ማጣራቶችን ስለማደርግ ምርጫውን ለአንድ ወር አራዝሙ የሚል ቀጭን ትዕዛዝን ያዘለ ደብዳቤ መላኩን ተከትሎ ምርጫው ለፌብርዋሪ 4 (እሁድ ጥር 27 2010ዓ.ም) መተላለፍ አይቀሬ እንደሆነ ነው እየተነገረ ያለው።
ፊፋ በዛሬው ዕለት የላከውን ደብዳቤ ተከትሎና ምርጫውን በተመለከተ ስብሰባ የተቀመጠው አስመራጭ ኮሚቴው ፊፋ የላከውን ደብዳቤ ተከትሎ ለሁለት የተከፈለ ሲሆን ምርጫው ይካሄድ ወይም ፊፋ ባዘዘው መሰረት ምርጫው በአንድ ወር ተራዝሞ ፌብርዋሪ ( እሁድ ጥር 27 2010ዓ.ም ) ይካሄድ በሚለው ዙርያ በአስመራጭ ኮሚቴው መካከል ዱላ ቀረሽ ክርክርና ክብረ ነክ ቃላት እስከመወራወር መድረሳቸው ነው የተሰማው።
ይህ በንዲህ እያለ ካፍ እና ፊፋ እንዳሳሰቡት ለፌዴሬሽኑ እንዳሳሰቡት ከዚህ የተለየ አቋም እሚያራምድ ከሆነ የምርጫ ታዛቢ እንደማይልኩ አሰርግጠው ተናግረዋል፡፡
አስመራጭ ኮሚቴውን ለሁለት የሰነጠቀው ስብሰባ ያለስምምነት ሲበተን አንደኛው ወገን ምርጫው መካሄድ አለበት ፊፋ ምን እግብቶት ነው አራዝሙ የሚለን ለአደጋ የሚያጋልፅ ፅንፍ ሲይዝ ሌላኛው ወገን በበኩሉ የፊፋን ውሳኔ ከማክበር ውጬ አማራጭ የለንም ለፊፋ ውሳኔ ተገዢ ልንሆን ይገባል ከዚህ ውጪ የሚሆን ነገር ሁሉ ሀገራችንን ዋጋ ያስከፍላታል በማለት የመጀመሪያውን ሃሳብ አጠንክረው በመቃወም በልዩነት መበተናቸውን ሀትሪክ ከታማኝ ምንጮቿ ያገኘችው መረጃ የሚጠቁሙት።
ለሁለት የተሰነጠቀው አስመራጭ ኮሚቴው በፊፋ ውሳኔና በተፈጠረው ችግር ዙርያ በቀጣይ የሚሰጠው መግለጫ ይጥበቃል።
- ማሰታውቂያ -
ፊፋ የላከው የደብዳቤ ይዘት ይሄን ይመስላል
1.የመጀመሪያው የመንግስት የስራ ሀላፊ ባስመራጭ ኮሚቴ ውስጥ ተካቷል በሚል ሲሆን
2.ለሁለት ተከታታይ ምርጫ በአሰመራጭ ኮሚቴ ውስጥ የተሳተፉ አባላት አሉ በሚል ሲሆን ሌላው 3ኛ ምክኒያት ከመንግስት ጣልቃ ገብነት ነፃ ነው ፡፡ ለማለት እንደማያስችልና የመንግስት ጣልቃ ገብነት ይታያል ፡፡በዚህም የምርጫ ሕጌ ተጥሷል በሚል ፊፋ ምርጫው እንዳይካሄድ በማለት ውሳኔውን ማስተላለፉ በደብዳቤው ተገልጿል፡፡ከዚህ በታች ሀትሪክ ጋዜጣ እና ድህረ ገፅ ደብዳቤውን በፎቶ በማስደገፍ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡