በተጠናቀቀው ውድድር ዓመት አጋማሽ የወልዋሎ እሰልጣኝነትን ከፀጋይ ኪዳነ ማርያም ተቀብለው ጥሩ እሚባል ጊዜያትን ያሳለፋት ዮሐንስ ሳህሌ ቀጣይ ዓመት ከወልዋሎ ጋር እሚያቆያቸውን ውል ተፈራርመዋል።
ትላንትና በይፋ በተከፈተው የኢትዮጵያ የክረምት ተጨዋቾች ዝውውር ሁለት ተጨዋቾችን ያጣው ወልዋሎ እዳዲስ ተጨዋቾችን ለማስፈረም በገበያው በንቃት እንደሚሳተፍ ይገመታል።
በ2010 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር የተሳካ ዓመት ያሳለፋት ዮሐንስ ሳህለ በቅርብ ዓመታት የደጋፊውን ፍላጎት ማሟላት የተቸገረውን ወልዋሎ የዋንጫ ተፎካካሪ ሊያደርጉት እንደሚችሉ ይጠበቃል።