በወቅቱ የተጨዋቾች ዝውውር ላይ በስፋት እየተሳተፋ ሚገኙት ደደቢት ሄኖክ ገብረመድህን እና ክብሮም አስመላሽን አስፈርመዋል።
የቀድሞው የደደቢት፣መቐለ 70 እንደርታና ዳሽን ቢራ ተጨዋች ሄኖክ ገብረመድህን ወደ ቀድሞ ክለቡ የመለሰውን ዝውውር አጠናቋል።የመሃል ሜዳ ተጨዋቹ ሄኖክ ጌታቸው ዳዊት መሀል ላይ ያላቸውን የተጨዋች አማራጭ ከማስፋቱ በተጨማሪ በወጣት ተጨዋቾች እየተገነባ ያለው ቡድንን ልምድ በማካፈል ሊያግዛቸው እንደሚችል ይገመታል።
ሌላኛው ፈራሚ ከዚህ በፊት ለመቐለ 70 እንደርታና ስሁል ሽረ የተጫወተው ክብሮም አስመላሽ ነው።የመስመር አጥቂው ክብሮም ደደቢት መቀላቀሉን ተከትሎ ከቀድሞ አሰልጣኙ ጌታቸው ዳዊት ጋር በድጋሜ ሚገናኝ ይሆናል።