የወቅቱ የተጨዋቾች መስኮት ዝውውርን ዘግይተው በመቀላቀል ስድስት አዳዲስ ተጨዋቾችን ያስፈረሙት ደደቢቶች ቃልኪዳን ገዛሀኝ አና ዓብዱልበሰጥ ከሚል በማስፍረም የፈራሚዎቻቸውን ቁጥር ስምንት አድርሰዋል።
በቅርቡ ከአናት ክለቡ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በስምምነት የተለያየው ቃልኪዳን ገዛሀኝ የጌታቸው ዳዊት ስብስብን ሊቀላቀል ችሏል።ባለፋት ዓመታት ከኢትዮጵያ ቡና ሁለተኛ ቡድን አድጎ ዋናው ቡድን ቀዋሚ ተሰላፊ እስከ መሆን የደረሰው ቃልኪዳን ሰመያዊዎቹ መሀል ላይ ያላቸውን አማራጭ ሊያሰፋላቸው እንደሚችል ይገመታል።
በተመሳሳይ ከኢትዮጵያ ሁለተኛ ቡድን ያደገው ዓብዱልበሰጥ ሌላኛው የደደቢት ፈራሚ ነው።ወደ ዋናው ቡድን አድጎ በቂ የመሰለፍ አድል ያላገኘው ዓብዱልበሰጥ ከሚል ወጣት ተጨዋቾች ላይ ትኩረት በማድረግ ላይ ያሉትን ደደቢቶችን ተቀላቅሏል።