በስሁል ሽረዎች አሸናፊነት ከተጠናቀቀው ጨዋታ በኃላ ሁለቱም አሰልጣኞች ሚከተለውን አስተያየት ሰጥተዋል።
አሰልጣኝ ሳምሶን አየለ (ስሁል ሽረ)
“ጨዋታው እንዳያችሁት ከዚህ በተሻለ በርካታ ጎሎች ገብተውበት መጠናቀቅ የነበረበት ጨዋታ ነበር።እንደ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ግን ፋሲል ከነማ ይዞት የመጣውን የጨዋታ አቀራረብ ቀድመን ተረድተን ስለነበረ ሀላፊነት ወስደን ከኃላ ቁጥራችንን በመቀነስ ከፍተኛ የሰው ቁጥርን እነሱ ሜዳ ላይ እንዲሆን አርገን በማጥቃት ላይ የተመሰረተ እንቅስቃሴ አርገን ሁለቱም 90 ደቂቃ ላይ ተጨዋቾቹ አተግብረውት ብዙ ግቦች ስተን ሁለት ግቦችን አግብተን ማሸነፍ ችለናል”
አሰልጣኝ ስዩም ከበደ (ፋሲል ከነማ)
- ማሰታውቂያ -
“ባጠቃላይ በዛሬው ዕለት ሽረ የነበራቸው አቋም በተለይ በመጀመርያው አጋማሽ ጥሩ ነው።ሜዳ ሞልተው ይጫወታሉ፣የነበራቸው የጨዋታ ፍላጎት መልካም ነገር ነው።በኛ በኩል ሁለተኛው አጋማሽ ላይ አሻሽለን ለመምጣት ሞክረናል፤ወደ ጨዋታችን እየተመለስን ባለንበት ወቅት ጎሎች በአጋጣሚ የመጡት።በተለይ ሁለተኛው አጋማሽ ላይ የተሻልን ነበር የሚል ስሜት አለኝ ።ግብ ሲቆጠር ከአንድ ቦታ መነሻ አለው የተቆጠረው ግብ ትንሽ የበረኛችን መዘናጋት አለበት።ከዛ በኃላ የበለጠ የኛ ስሜት የመውረድ ነገር ይታያል ምክንያቱም የመጀመርያ ግብ ሲገባ ስድስት ደቂቃ ነበር የቀረው ከዛ በኃላ ለመነሳት እጅግ ይከብዳል።ባጠቃላይ ከዚህ ትምህርት ምንወስድበት ይሆናል”