THE BIG INTERVIEW WITH SURAFEL DANGACHEW
በይስሀቅ በላይ
- ማሰታውቂያ -
ሱራፌል ዳኛቸው፣ ይሄ ስም የወደፊቱ የእግር ኳሱ ትልቅ
ስም፣ የጋዜጦች የፊት ገፅን የሚያጣብብ፣
ሚዲያዎች ደጋግመው የሚያነሱት ስም
ለመሆን መንገዱን ጀምሯል፤ ገና ከወዲሁ
ከሁለትና ሶስት ጣት ባልዘለለ የጨዋታ
እድሜው “ሱራፌል ዳኛቸው” የሚለው ስም
በእግር ኳሱ መንደር ከፍ ብሎ መነሳት
ጀምሯል፡፡
ከዛሬ ሰባት አመት በፊት የኢትዮጵያ ብ/
ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ከ31 አመት በኋላ
በአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው መሪነት ሲያልፍ
ፊቱን አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ቀለም ተቀብቶ
በአዳማ ከተማ ጎናዳዎች ሲቦርቅ፣ሲጨፍር
የነበረው ታዳጊው ሕፃን ዛሬ ያ ታሪኩ
ተቀይሮ አድጎ ተመንድጎ የኢትዮጵያ ብ/
ቡድንን ወደ ካሜሩን የአፍሪካ ዋንጫ
የማሳለፉ አደራ በትከሻው ላይ የወደቀ
መሆኑ የስኬቱን ፍጥነት ማሳያም ነው፡
፡ በወቅቱ የ10ኛ ክፍል ተማሪ የነበረውን
ሱራፌል ዳኛቸው የኢትዮጵያ ብ/ቡድን
በኮትዲሾዋር ላይ ወርቃማ ግብ አስቆጥሮ
ሲያሸንፍ ያኔ ለዚህ ይበቃል ብሎ የገመተም
የጠረጠረም አልነበረም፡፡ ሱራፌል ግን
በጣም አጭር በሆነ ጊዜ ነገር ግን በጣም
የፈጠነ ስኬቶችን በማስመዝገብ ሀገሪቱ
አሉኝ ብላ ከምትጠራቸው ተጨዋቾች
አንዱ ለመሆን በቅቷል፡፡ ከሶስት አመታት
ባልዘለለ የእግር ኳስ ህይወቱ የጥሎ ማለፉ፣
የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫን ክብርና ለኮከብ
ተጨዋችነት የመታጨት፣ ለብ/ቡድን ታላቅ
ኃላፊነት መብቃት ከብርሃን በቀደመ ፍጥነት
እየተጓዘ ያለውን የሱራፌል ዳኛቸውን
ህይወት ሊያስቃኘን የሀትሪክ ጋዜጣ
ኤክሲኪዩቲቭ ኤዴተር ጋዜጠኛ
ይስሀቅ በላይ ብዕሩን ከወረቀት ጋር
አስማምቶ ለለመሆኑ ሱራፌል ዳኛቸው
ማነው?ብሎ ጠይቆ የወጣቱን ህይወት
ሊያስቃኘን ከዚህ በታች ባለው መልኩ
አጠናክሮታል፡፡
ሀትሪክ፡- ..ቅድሚያ ምንድነው የሚ
ባለው…?…እንኳን ደስ አለህ…? ወይስ…
ለቃለ-ምልልሱ ፍቃደኛ ስለሆንክ ከልብ
አመሰግናለሁ…?…ግን ቆይ ቆይ…ከዚያ
በፊት ከኮትዲቯር ጋር በነበረው ጨዋታ
ላይ ግብ ካስቆጠርክ በኋለ ኳሷን ሆድህ
ውስጥ ከተህ ነው ደስታህን የገለፅከው…
ይሄን ያደረከው ለነፍሰ ጡርዋ ባለቤቴ
ማስታወሻነት ይሁንልኝ ለማለት ነው?
ሱራፊል፡- …(በጣም ያላባራ ሳቅ)…
ማን ነገርህ…?…(አሁንም ሳቅ)…በጣም
የምትገርም ሰው ነህ… አዎን በወቅቱ ባለቤቴ
ነፍሰ ጡር ስለነበረች…ግቡን ለእሷና ለአዲሱ
ልጄ ማስታወሻ መሆኑን ለማሳየት ነበር ያንን
ያደረኩት…፡፡
ሀትሪክ፡- …አሁን እንኳን ደስ አለህ…
እንኳን ለዚህ ክብር በቃህ ማለት እችላለሁ
አይደል…ሱሬ…?
ሱራፊል፡- …(በጣም ሳቅ)…አዎን
ይቻላል… እንኳን አብሮ ደስ አለን.. (ሳቅ)…
ሀትሪክ፡- …እንኳን ደስ ያለህ
ያልኩት ኮትዲቮዋርን ስላሸነፋችሁ ብቻ
እንዳይመስልህ በቅርቡ ኮትዲቯርን
ባሸነፋችሁ ማግስት የሴት ልጅ አባት
መሆንህ ስለሠማሁ ጭምር ነው…?
ሱራፊል፡- …በጣም አመሰግናለሁ…
በዚህች ምድር ላይ እንደ እኔ ደስተኛ ሆኖ
ያሳለፈ የለም ኮትዲቯርን በማሸነፍ ከህዝባችን
ጋር እየተደሰትን ባለበት ሰዓት ባለቤቴ ደግሞ
ሴት ልጅ አሣቅፋኛለች፤በስሜ የምትጠራ
የአንዲት ሴት ልጅ አባት የመሆን ማዕረግም
(ክብር) ስላገኘሁ የደስታዬ መጠን ከልኩ
አልፏል፡፡ ኮትዲቯርን አሸንፈን ከህዝቡ ጋር
ተደስትን በታሪክ የመጀመሪያ ኢንተርናሽናል
ጎሌን ታላቅዋ ኮትዲቯር ላይ አስቆጥሬ በደስታ
በሰከርኩበት ሰዓት ሌላ ትልቅ ስጦታ ከባለቤቴ
አገኘሁ፤ በደስታ ላይ ደስታ…በቃ ምንም
ልበልህ እንደ እኔ እድለኛ ሰው የለም…፡፡
ሀትሪክ፡- …ይህቺን ምድር በቅርቡ
የተቀላቀለችውን ሴት ልጅህን ስም
አወጣችሁላት…?…ማን ተባለች…?…
ምንአልባት ከጨዋታው ወይም ከጎልህ ጋር
የተያያዘ ነገር ካለ ብዬ ነው…?
ሱራፊል፡- …(ሣቅ)…አይ እስከአሁን
ያወጣንላት ስም የለም፤ባለቤቴ የወለደችው
የሚካኤል ዕለት ነው፤ ገና 12ኛ ቀንዎ
ነው።(ያነጋገርነው ሐሙስ ነው) ልጅ
በማግኘታችን በመደሰቱ ላይ ነው ያተኮርነው፤
እንግዲህ በቀጣይ ነው ወደ ስም ማውጣት
የምንሄደው…(ሣቅ)…
ሀትሪክ፡- …እንዲህ ያጣደፊው የዛሬዋ
ባለቤቱ ምን ያህል በፍቅርዋ ብትማርከው
ነው…የሚሉ አሉ ምን ትላለህ….?
ሱራፌል፡- … (በጣም ሳቅ)…አንድ
እውነት ልንገርህ የእሷን ፍቅር መቋቋም
አልቻልኩም፤ ከእሷ ጋር ወልጄ ከብጄ በአንድ
ጣሪያ ስር አብሮ የመኖር ጉጉቴ አጣድፎኝ
ነው ቶሎ ወደ ትዳር የገባሁት፡፡ ከዚህ ሌላ
አሁን ደግሞ ጊዜው በጣም ከባድ ነው…
አላማህን ለማሳካት ቶሎ ሰብሰብ ማለት
በጣም ይጠቅማል፤እሷ በጣም ስለምታስብልኝ
አሁን ላለው ህይወቴ መሠረት የጣለችልኝ
በመሆኑ ማመንታት አልፈለኩም፤ቶሎ ወስኜ
ትዳር ልንመሰርት ችለናል፡፡
ሀትሪክ፡- …እስቲ የልጅ አባት
ያደረገችህን ባለቤትህን አስተዋውቀኝ…?…
በአራዳ ቋንቋ ቀድሞ የጠበሰውስ ማን
ነው?
ሱራፌል፡- …(በጣም ሳቅ)…ቀድማ
የጠበሰችኝ እሷ ናት…(ሣቅ)…ባለቤቴ ሜሮን
ሠለሞን ትባላለች፤ በእድሜ በጣም ለጋ
በአስተሳሰብዋ ግን በጣም ትልቅ የሆነች
ልጅ ናት፤ አሁን ገና 21ኛ አመቷን ለመያዝ
እየተንደረደረች ነው፡፡ የተዋወቅነው ማርክ
ዙከርበግ በፈጠረው ፌስ ቡክ አማካይነት
ነው (በጣም ሣቅ)…በፌስ ቡክ የተጀመረው
ትውውቅ ነው አድጎ ትዳር ለመመስረትና ልጅ
እስከመውለድ ያደረሰን፤ፌስ ቡክን ለቁምነገር
ተጠቅመንበት ነው ለዚህ የበቃነው (ሣቅ)…
ሀትሪክ፡- …ብዙዎች ትዳርና ተጨዋ
ችነት አብርው አይሄዱም በሚል ትዳርን
ሲሸሹ ሲገፉት ይታያል… ሱራፌል እንዴት
ይሄን አመለካከት ሰብሮ በጊዜ ወደ ትዳር
ለመግባት ወሰነ…?
ሱራፌል፡- በጣም ትልቅ ነገር ነው
ያነሳኸው፤ በእኛ ማህበረሰብ ትዳርና
ተጨዋችነት አብሮ አይሄድም የሚል አሣሪ
አመለካከት አለ፤ በእርግጥ እኔም ይሄን
አባባል እሠማ ነበር፡፡ ነገር ግን ከተማመንክና
መቁረጥ ከቻልክ ትዳር ይበልጥ ጠቃሚ
መሆኑን በመረዳትና በማመኗ ለአፍታም
ቢሆን ወደ ኋላ ማለትን አልመረጥኩም፡
፡ ውስጡ ገብቼም ሳየው አንዳችም ችግር
አላየሁበትም፡፡ እንደውም ጥቅሙ ነው
የታየኝ፤ በዚህ ዘመን በትዳር ታስረህ
መጫወት ብዙ ጥቅም ነው ያለው፡፡ ከምንም
በላይ ራስህን ትጠብቃለህ፡፡ በፕሮግራም
የምትመራ ሰውም እንድትሆን ያደርግሃል፡
፡ ከአልባሌ ቦታ እንድትርቅም ያደርግሃል፡፡
ስለዚህ በጊዜ መሰብሰቡን መርጫለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- እስቲ ስለ እግር ኳስ
አጀማመርህ እናውራ…ከመርቲ ጀጁ
የተነሣው የሱራፊል የእግር ኳስ ህይወት
መነሻው ምንድነው?
ሱራፊል፡- …ተወልጄ ያደኩት
እንዳልከው መርቲ ጀጁ ነው፤ በእኛ አካባቢ
ብዙም የእግር ኳስ እንቅስቅሴ የለም፤
በልጅነት ለስሜት ከ ም ት ጫ ወ ተ ው
ውጪ፡፡ ያም ቢሆን ግን ሱልጣን መሀመድና
ኃይሌ ካሱ የሚባሉ አሰልጣኞች ነበሩ…
እነሱ በሠፈር ደረጃ ያሰለጥኑን ነበር፡
፡ እኔኔ እንደውም ወደ እግር ኳስ የሳበኝ
ስለ ቡናና ቅ/ጊዮርጊስ የምሰማቸው ዜናዎች
ናቸው፤ቡና፣ ጊዮርጊስ እየተባለ ዜና ስሰማ
በውስጤ ትልቅ የመነሳሳት ስሜት ይፈጠር
እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ በተለይ የቡናንና
የጊዮርጊስን ደጋፊዎች በቴሌቪዥን መስኮት
ስመለከታቸው ምነው እኔም አንድ ቀን በዚህ
ደጋፊ መሀል ለአንድ ሰከንድም ቢሆን ብቆም
ብዬ ሁሉ እመኝ ነበር…(ሣቅ)…ከዚህ ውጪ
ብዙም በአከባቢያችን ኳስ የለም፤ለተስፋ
ቡድን ሱልጣን እያሰለጠነን እየተጫወትን ነው
ወደ ኳስ የተሳብኩት፡፡
ሀትሪክ፡- …በልጅነትህ እያደነክ እንደ
እሱ ለመሆን እየተመኘህ ያደከው…ተፅዕኖ
የፈጠረብህ ተጨዋች አለ…?
ሱራፊል፡- …እንዳልኩህ ነው…ብዙም
የማየት እድሉ አልነበረኝም… አልፎ አልፎ
ከማገኘው አጋጣሚ ውጪ፤ ያም ቢሆን
ግን እኔም በአማካይ ቦታ ስለምጫወት
አስታውሳለሁ… ለሽመልስ በቀለና በተለይ
ለዳዊት እስጢፋኖስ በጣም የተለየ ስሜት
ነበረኝ፡፡ ወደ አዲስ አበባ ከቤተሰቤ ጋር
ስሄድ ስታዲየም እየገባሁ በተለይ የዳዊት
እስጢፋኖስን አጨዋወት እመለከት በጣምም
አደንቀው ነበር፡፡ ሽመልስንም ብዙም ባላየውም
ኳስ አያያዙ አጨዋወቱ በጣም ይማርከኝ
አደንቀውም ነበር፡፡
ሀትሪክ፡- .. በዚህ ደረጃ እያደነክ
ካደከው ሽመልስ በቀለ ጋር በብ/ቡድን
ደረጃ አብረኸው የመጫወት እድል ስታገኝ
ምን ተሰማህ?
ሱራፊል፡- … (ሣቅ)… ህልም ታውቃለ ህ?…በቃ የህልም ነው ያህል የሆነብኝ…የሆነ
የማታምነው ነገር አለ አይደል? ልክ እንደዛ…
(ሣቅ)… በቃ እውነት ሆኖ ግን አምነህ
ለመቀበል የምትቸገረው ነገር የለም?…
እንደዛ በልጅነት እዕምሮዬ ሳደንቀው ከነበረው
ሽመልስ ጋር ያውም በብ/ቡድን ደረጃ? እውነት
እውነትም አልመሰለኝም፡፡ አስታውሳለሁ
የመጀመሪያ ቀን ከሽመልስ ጋር የተገናኘነው
ምግብ ላይ ነው፤ እሱ ገና ከውጪ መጥቶ ነው
ብ/ቡድኑኑ የተቀላቀለው…ለማመን ከመቸገሬ
የተነሣ ምግቤን ትቼ ሽመልስን ዝም ብዬ አይን
አይኑን እመለከተው ነበር…(ሣቅ)…አስሬ
ብቻዬን “ወይ ጉድ እውነት እኔም ለዚህ ክብር
በቅቼ ሽመልስን ከሚያክል ተጨዋች ጋር
አብሬ የምጫወትበት እድል ተፈጠረ…?…
የማይታመን ነው እያልኩ ብቻዬን አወራ…
እሱንም ዝም ብዬ እመለከተው እንደነበር
አስትውሳለሁ…፡፡
ሀትሪክ፡- …በልጅነትህ ስታደንቀው
ከነበረው ሽመልስ ጋር ያውም በሀገር
ደረጃ አብረኸው የምትጫወትበት እድል
ብቻ ሣይሆን ብ/ቡድኑም በኮትዲቯር ላይ
ወርቃማ ድል ሲጎናፀፍ አንተም ስታደንቀው
የነበረው ሽመልስም ባስቆጠራችሁት ግብ
ብ/ቡድኑ ነው፤ይህ ግጥምጥሞሽስ ምን
ስሜት ፈጠረብህ….?
ሱራፊል፡- …በቃ ምን ልበልህ…
ልቅ ቦታ ከምትሰጠው ተጨዋች ጋር
ባስቆጠርናቸው ግቦች ኮትዲቯርን የሚያክል
ቡድን ማሸነፋችን…የእኔም ስም ከእሱ ጋር
አብሮ በመጠራቱ በቃላት የማልገልፅልህ
የደስታ ስሜት ነው የተሰማኝ፡፡
ሀትሪክ፡- … ሽመልስን ስታገኘው ስታደንቀው እንዳደክ ያወራኸው አጋጣሚ
ስ አለ… ?
ሱራፊል፡- …(እንደመሣቅ እያለ)…
እኔ በባህሪዬ ብዙም ደፋር አይደለሁም…
ሽሜንም በጣም የማከብራት ሲኒየር ተጨዋች
በመሆንዋ በዚህ ጉዳይ ለማውራት ድፍረት
አላገኘሁም፡፡ ግን አስታውሳለሁ እኔና እሱ
ለመጀመሪያ ጊዜ የተነጋገርነው ትሬይኒንግ
ላይ በሰጠችኝ ምክር ነው…እኔ ብዙውን
ጊዜ የኬርለስነት (የቸልተኝነት) ባህሪ አለኝ፡
፡ ይሄንን ሽሜ ተመልክታ “እንደዚህ
ቸልተኛ መሆን የለብህም… ሲሪየስ ሆነህ
ነው መጫወት ያለብህ፤ አይዞህ በርታ”
ብሎ አበረታቶኛል በወቅቱ ሽመልስ እንደዛ
ሲመክረኝ ቀና ብዬ አይኑን ለማየት እንኳን
ድፍረት አላገኘሁም… አንገቴን አቀርቅሬ ነው
የሚለኝን ሰምቼ እሺ ያልኩት፡፡ ይሄ የሆነው
ለምን መሰለህ ሽሜን በጣም ስለማደንቀውና
ስለማከብረው ነው፡፡ አሁን ግን እየተላመድን
በደንብ እየተግባባን መጥተናል… በዚህም
በጣም ደስ ብሎኛል፡፡
ሀትሪክ፡- …ለኢትዮጵያ ብ/ቡድን
የመመረጥ እድል ያገኘኸው በአጭር ጊዜ
ነው…በዚህ ደረጃ ሀገሬን እንዳገለግል
ጥሪ ይደረግልኛል ብለህ አስበህ ነበር…
ስትጠራስ ምን ተሰማህ…?
ሱራፊል፡- …እንዳልከው ነው…ለብ/
ቡድን የመጠራት እድሉን ያገኘሁት
አጭር በሚባለው የጨዋታ ዘመኔ
ነው፤አዳማ በ2009 የመጫወት
እድል አገኘሁ…በ2010 በጣም
የተሻለ እድል አገኘሁ…በ2011
ደግሞ ወደ ፋሲል ሄጄ መጨወት
ቻልኩ…ይሄን ስታይ ለብ/ቡድን
የተጠራሁት በፍጥነት ነው ይሄ
በጣም አስደስቶኛል፡፡ ለብ/ቡድን
የመጫወት ህልም ቢኖረኝም
በዚህ ፍጥነት ይሆናል ብዬ ግን
አላሰብኩም።የሚገርምህ ነገር
ለU-20 እና U-23 ብ/ቡድንም
ተመርጬ ተጫውቻለሁ፡፡ ይሄ
የሚያስደስት ቢሆንም ለዋናው
ቡድን እነ ሽመልስ በቀለን
ከመሳሰሉ ታላላቅ ተጨዋች ጋር
የመጫወት እድል የሚያስገኝ ጥሪ ሲደረግልኝ
ደስታዬን ልነግርህ አልችልም በጣም ነው
የተደሰትኩት፤ሀገርን ከማገልገል በላይ ምን
የሚያስደስት ነገር አለ፡፡ መጫወቱን ተወው
ተመልካቹ ፊት የሀገርህን የህዝብ መዝሙር
ስትዘመር ማልያውን ስትለብስ ራሱ የሆነ
የሚነዝርህ፣ የማትገልፀው ልዩ የደስታና
የኩራት ስሜት ይሰማሃል …እኔም የተሰማኝ
ይሄ ነው፡፡
ሀትሪክ፡- …አሁን ያለው የብ/ቡድን
ስብስብ እንዴት ነው የምትገልፀው…?
ሱራፊል፡- …የሆነ ታሪክ ለሀገሩ
ለመስራት የጓጓ…ውጤት ለማስመዝገብ
የተራኩ ተጨዋቾች ያሉበት ስብስብ
ነው፤በአብዛኛው የቡድኑ ተጨዋች ወጣቶች
ናቸው…ለማሸነፍ ያላቸው ስሜት በቀላሉ
የሚገለፅ አይደለም፡፡ ሁላችንም በጨዋታ
ዘመናችን ለሀገራችን አንድ ታሪክ ሠርተን
የማለፍ፣ ህዝባችንን የማስደሰት ትልቅ
ጉጉት ነው ያለን።እንደ ሽመልስ በቀለ አይነት
ልምድን፣ ችሎታንና ፀባይን አጣምሮ የያዘ
ታሪክን የሰሩ ተጨዋቾች ስላሉበት ከእነርሱ
ብዙ ልምዶችን እያገኘን ጠንክረን እየሰራን
ነው፡፡ በአጠቃላይ ስብስባችን ጥሩ ነው…
በጊዜ ሂደት ልምድንም እያካበትን እየመጣን
በመሆኑ ሁሉም ነገር ጥሩ ነው፡፡
ሀትሪክ፡- …አሁን…አሁን ሱራፊል
የሚለው ስም…በብሔራዊ ቡድን ውስጥ
ጎልቶ የሚሰማ…ከፍ ብሎ የሚጠራ
ስም እየሆነ ነው፣ ይሄስ ምን ስሜት
ፈጠረብህ…?
ሱራፊል፡- …በዚህ ደረጃ መነሳቴ ደስ
ያሰኛል…ክብርም ኩራትም እንዲሰማኝ
ያደርጋል፤ግን ለሀገሬ ገና ምንም ያልሰራሁ
ገና ብዙ መስራት የሚጠበቅብኝ መሆኑን ብቻ
ነው አሁን የማውቀው፡፡
ሀትሪክ፡- …ኮትዲቯሮች የአርሴናል
ውዱ ተጨዋች ኒኮላስ ፔፔና ሌሎች
ፕሮፌሽናሎች ጎን መጫወት ብቻ ሣይሆን
እነሱ ላይ ግብ አስቆጥረህ ማሸነፋችሁ
በውስጥህ የፈጠረውስ ምንድነው… ?
ሱራፊል፡- …ኦ…በጣም ልዩ የሆነ
የደስታ ስሜት ነው የሚሰማህ…እንዳልከው
የኮትዲቯር ብ/ቡድን የአህጉራችንን ብቻ
ሣይሆን የአለማችንን ታላላቅ ተጨዋቾች
የያዘ ብ/ቡድን ነው…ሁሉም ፕሮፌሽናሎች
ናቸው፤እነዚህን ተጨዋቾች እኮ እንኳን
ግብ አስቆጥሬ ልናሸንፋቸው ቀርቶ ገንዘብ
ከፍለን ቁጭ ብለን በቴሌቪዥን መስኮት
ስንመለከታቸው የነበሩ ተጨዋቾች ናቸው፤
እነዚህን በዚህ ደረጃ ስትመለከታቸው የነበሩ
ተጨዋቾችን ማሸነፍ ያውም ግብ አስቆጥረህ
በጣም የተለየ ደስታ ነው የሚያጎናፅፍህ
፤ከዚህ በኋላ እኔም ብ/ቡድኑም ኮትዲቯር
ስትነሣ አብሮ የሚነሣ ትልቅ ታሪክ ስላፃፍን
በጣም ደስ ብሎኛል፤ደስታዬም ወደር የለም፡፡
ሀትሪክ፡- …የኮትዲቯርን ብ/ቡድን
ካሸፋችሁ በኋላ ለ2021 የካሜሩን የአፍሪካ ዋንጫ የማለፍ ተስፋችሁ ተመልሷል፤ ዛሬ
ላይ ሆነህ የካሜሩኑን የአፍሪካ ዋንጫ
ታልማለህ?
ሱራፊል፡- …በጣም እንጂ…!…ህልም
ከሌለህማ ምኑኑ ሰው ሆንከው…?…ማለም
አለብህ …ህልምህን ለማሳካትም ጠንክረህ
መስራት አለብህ…እኛም እያደረግን ያለነው
ይሄንኑ ነው፡፡ የኮትዲቯር ድል አይቻልም
የተባለው ነገር እንደሚቻል ያሳየንበት ጠንክረን ከሰራን የምናስብበት
ደረጃ መድረስ እንደምንችል የሚጠቁም
ነው፡፡
ምክንያቱም ይሄ ጨዋታና
ውጤቱ የምድቡ ትልቅ ጨዋታና
ትልቅ ዋጋ ያለውም ውጤት ነው
ያስመዘ ገብነው…ከዚህ አንፃር
የካሜሩንን የአፍሪካ ዋንጫ
እናል ማለን… ግን ህልም
ብቻውን የትም ስለማያደርሰን
ህልማችንን እውን ለማድረግ
ጠንክረን እን ሠራለን፡፡
ሀትሪክ፡- …
ኮትዲቯርን በማሸነፋችሁ
ውጡቱ ራሳችሁን
የተለያችሁ አድርጋችሁ
እንድታስቡ
ያደርጋል…?…
ያኩራራል…?
ሱራፊል፡- …
በእርግጥ ድሉ ትልቅ
ውጤት ነው…ግን ይሄ
ድል የተለየን አድርገን
እንድናስብ እንድንኩራራ
እያደርገንም… ድሉ ለቀጣይ
ጨዋታ የሞራል ስንቅ ይሆነናል
እንጂ አያኩራራንም፤ ከዚህ በዘለለ
ግን ውጤቱ ራሳችንን ዝቅ
አድርገን እንዳናስብ ለካስ አቅም
አለን?አቅማችንን አውጥተን
ከተጫወትን የተሻልን ልንሆን
እንችላለን ብለን እንድናስብ
ከማድረግ ውጪ አያኩራራንም፡፡
ሀትሪክ፡- …አሁን አንተ
የ2021ዱን የአፍሪካ ዋንጫ
እያለምክ ነው፤ከሰባት አመት
በፊት የኢትዮጵያ ብ/ቡድን ከ31
አመት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ
ሲያልፉ ሱራፌል የት ነበር?
ሱራፊል፡- …ኡ…(በጣም
ሳቅ)…ያኔማ ገና የ10ኛ ክፍል
ተማሪ የማትሪክ ተፈታኝ ነበርኩ፤
ሱራፌል ዳኛቸው የሚለው ስም
ገና ከሠፈር ስላልወጣ በእግር
ኳሱ መንደርም አይታወቅም፡፡
የሚገርምህ ብ/ቡድኑ ከሱዳን ጋር
የመጨረሻውን ጨዋታ አዲስ አበባ
ላይ ሲያደርግ እኔና ጓደኞቼ እንዲሁም
የአዳማ ልጆች አረንጓዴ፣ቢጫና ቀይ
ቀለም ፊታችንን ተቀብተን ነበር
ጨዋታውን ስንከታተል የነበረው፡፡ ልክ ጨዋታው ሲያልቅና ማለፋችን ሲረጋገጥ
እንዴት በደስታ እንደሰከርን እንዳበድን
ዛሬ ላይ አላስታውሳለሁ፤ አዳማ ፖስታ
ቤት አደባባይ አለ እዚያ ወጥተን በጭፈራ
እንደቀወጥነው አስታውሳለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- …ከዛሬ ሰባት አመት
በፊት ብ/ቡድኑ ለአፍሪካ ዋንጫ ሲያልፍ
ቀለም ተቀብቶ ሲጨፍር፣
ሲደሰት የነበረው
ሱራፊል…ዛሬ ደግሞ
ባለ ተራ ሆኖ ብ/
ቡድኑን ለአፍሪካ
ዋንጫ የማሳለፍ
ትልቅ ኃላፊነት
ትከሻው ላይ
የወደቀበት ጊዜ
ላይ ደርሷል…
ይሄንን እንዴት
ታነፃፅረዋለህ፡
፡?
ሱራፊል፡
– …በጣም
ከባድ ነገር
ነው… ይሄንን
ለማነፃፀርም
ለመግለፅም
ቃላቶች
ያጥሩኛል፤
እንኳን በእውን
በህልምም
የማይሆን
የሚመስል ነገር
ነው የተፈጠረው፡፡
ወደ ኋላ ተመልሼ ሳስታውሰው እውነት
እኔ ሱራፌል ነኝ ለዚህ ትልቅ ክብር
የበቃሁት?ብዬ የፈጠረኝ
አምላኬን አመሰግነዋለሁ፡፡ የ100
ሚሊዮንህዝብ ውክልና ለመሸከም
መብቃት በእውነት ዳግም መወለድ ነው፡፡
በውጤት ማጣት ስሜቱ የጎዳን ህዝብ
ለማስደሰት አደራ ከተሰጣቸው ውስጥ
አንዱ ለመሆን በመብቃቴም አምላኬን
አመሰግነዋለሁ፡፡ ትላንት እነ አዳነ፣ሳላህዲንና
ሌሎች የብ/ቡድን ተጨዋቾች በዘመናቸው
ትልቅ ታሪክ ሠርተው አደራውን ለእኛ
አስሪክበው ሄደዋል፡፡ እኛ ደግሞ በተራችን
የእነሱን ታሪክ በመድገም የሀገራችንን
ስም ከፍ ለማድረግ ወደ አፍሪካ ዋንጫ
በመመለስ ታሪክ ለመስራት የምንችለውን
ሁሉ እናደርጋለን፤ሌላው ትናንት እነ
አዳነ ሣላህዲንና ሌሎች የቡድኑ አባላት
በስኬታቸው ቀለም ተቀብተን አደባባይ ላይ
ወጥተን እንድንጨፍር እንዳደረጉን ሁሉ
እኔም በተራዬ ሌሎች እንደዚህ እንዲሆኑ
እጥራለሁ… (ሣቅ)…
ሀትሪክ፡- …የመጀመሪያ ክለብህ አዳማ
ከተማ ነው…አገባብህ እንዴት ነበር…?
ሱራፌል፡- …ወደ አዳማ ዋናው ቡድን
የገባሁት ከ U-17 (ከ17 አመት በታች)ቡድን
ነው፤ በወቅቱ የክለቡ አሰልጣኝ የነበረውአ
ሸናፊ በቀለ ነው ያሳደገኝ…ከዚያበፊት ግን
ወደ አዳማ ከተማ ከመምጣቴ በፊት ማለት
ነው በዶ/ር ኃይሉ ስር በሚሰለጥነው የታዳጊ
ቡድን ውስጥ እሠራ ነበር፡፡ ዶ/ር ኃይሉ
ብሔራዊ ሊግ ለሚጫወተው የአዲስ ከተማ
ክፍለ ከተማ ቡድን ወስዶኝ ልጅ ስለሆነ
ልምድ ያግኝ ብሎ ትሬይኒንግ እሰራ ነበር፡
፡በዚህ መንገድ ከአሠልጣኝ ፈቀደ ቲጋ
ጋር ስሰራ ከአንድ አመት በኋላ ግን ወደ
አዳማ ከተማ U-17 ቡድን መጣሁ፡ አዳማ
ታዳጊ ቡድን እንደመጣሁ በ2008 ዓ.ም
የተካሄደው ከ17 አመት በታች ውድድር
ሻምፒዮን በመሆን የመጀመሪያ ዋንጫዬን
አነሳሁ፡፡ በታዳጊ ቡድን ባሳየሁት ብቃት
እንዳልኩህ በአመቱ በአሸናፊ በቀለ ምክንያት
ወደ ዋናው ቡድን አደኩ፤በ2009 በዋናው
ቡድን የመጫወት ዕድልም አገኘሁ፤ በ2009
ደግሞ በአዳማ የተሻለ ጥሩ ጊዜ አገኘሁ፡፡
ሀትሪክ፡- …በአዳማ የነበረህን ቆይታ
እንዴት ታስታውሰዋለህ…?
ሱራፌል፡- …በአዳማ በጣም አሪፍና
የማይዘነጋ ጊዜ ነው ያሳለፍኩት…በአጭር ጊዜ
ውስጥ የደጋፊውንም ልብ ማሸነፍ የቻልኩበት
ክለብም ነው፡፡ አዳማን ከተማውንም ክለቡንም
ከልቤ ነው የምወደው፤ለዛሬው ሱራፌል
መወለድ ምክንያትና ትልቁ መሰረት የሆነ
ክለብም በመሆኑ ሁሌም በውስጤ የሚኖር
ትልቅ ፍቅር ያሳለፍኩበት ክለብ ነው፡፡
ሀትሪክ፡- …በአዳማ ያላሳካሀት
የሚቆጨኝ ነገር የምትለው አለ…?
ሱራፌል፡- … እንዳልኩህ አዳማ
ከታች አሳድጎ ለዛሬው ማንነቴ
ምክንያት የሆነኝ ክለብ ነው፣
ይሄንን ውለታ ለፈፀመልኝ
ክለብና ደጋፊ ሁሌም ስታወስ
የምኖርበትን ታሪክ ወይም
ድል አስቀምጬ ባልፍ በጣም
ደስ ይለኝ ነበር፡፡ በተለይ
ምርጥ ለሆኑት ደጋፊዎችና
ለክለቡ የፕሪሚየር ሊጉን
ዋንጫ አበርክቼ ብወጣ በጣም
እደሰት ነበር፡፡ ይሄንን አለማሳካቴና በአዳማ
አንድ ታሪክ ሳልሠራ መውጣቴ በጣም ነው
የሚቆጨኝ፤ከቡደኑ ጋር የሊጉን ዋንጫ
አግኝቼ ብወጣ እደሰት ነበር፡፡ ምክንያቱም
በጣም ምርጥ ተፎካካሪ ቡድን ነው የነበረን
በወቅቱ…በክለቡ ውስጥ ጥሩ ጥሩ አስተማሪ
የሆኑ ሲኒየር (ነባር) ተጨዋቾች እንደእነ
ታፈሰ ተስፋዬ፣ ብሩክ ቃልቦሬ፣ አዲስ ህንፃ፣
ተስፋዬ (ጃምቦ)፣ ምኞት ደበበን የመሳሰሉ
ለወጣቶች የሚያስቡ ምርጥ ተጨዋቾች
የነበሩበት ቡድን ነበር፤ ከእነዚህ ተጨዋቾች
ጋር ይሄን ታሪክ አፅፌ ብወጣ በጣም
እደሰት ነበር…እሱን ባለማሳካቴ ካልተቆጮሁ
በስተቀር በአዳማ በጣም ምርጥ ጊዜ ነበረኝ፡፡
ሀትሪክ፡- …አዳማዎች አንተን ብዙ
ተስፋ የተጣሉበትና አይኑን በድንገተኛ
ጉዳት ካጣው ታከለ አለማየሁ ጋ በማነፃፀር
“ሱራፌል ታከለን ያስታውሰናል” በማለት
ደጋፊዎች ከእሱ ጋር ያነፃፅሩሃል.. ይሄን
ታውቅ ነበር…?
ሱራፌል፡- …ትክክል ነህ…ደጋፊዎቹ
ብቻ ሣይሆኑ አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለም
ራሱ “አንተ ለእኔ የታከለ ምትክ ነህ” ይለኝ
ነበር፤ምንድነው የሆነው መሠለህ በጣም
የምናደንቀው የምንወደው ታከለ አለማየሁ
በተጎዳበት ሰዓት እኔ ገና ከቢ ማደጌ ነበር…
ብዙም ስለ ፕሪሚየር ሊጉ እውቀቱም
ልምድም አልነበረኝም…በዚህ ሁኔታ
ውስጥ እያለሁ ታኬ ጉዳት ደረሰበት…
ሁላችንም ደነገጥን፣ ተረበሽን፡፡ ያን አጋጣሚ
ዛሬ ተመልሼ ማስታወስ ይከብደኛል…
ምክንያቱም ሁላችንም መጥፎ ስሜት ውስጥ
ነበረን፤በአጠቃላይ በቡደኑ ላይ መጥፎ
አጋጣሚ ነበር የተከሰተው፡፡ በዚህ ሁኔታ
ውስጥ እያለን ሁሌም “የታከለ ምትክ ነህ”
ስባል የበለጠ ነገሮች ሁሉ ከበዱኝ፤ በተለይ
አሰልጠኛችን አሽናፊ በቀለ “አንተ ለእኔ
የታከለ ምትክ ነህ” ብሎ እሱ የሚለብሰውን
7 ቁጥር ማልያ ሲሰጠኝ የበለጠ ተጨነኩ፣
ተረበሽኩ፣ በጣምም ፈራሁ፡፡ እኔ መጀመሪያ
የምለብሰው 14 ቁጥር ነበር… አሸናፊ “አንተ
የእሱ ማስረሻ ነህ” ብሎ 7 ቁጥር ማልያውን
ሲሰጠኝ እውነቱን ልንገርህ አልቀበልም ነበር
ያልኩት…
ሀትሪክ፡- …ይሄን ያህል?… ለምን
አልቀበልም አልከው…?
ሱራፌል፡- …ምክንያቱም በሰዓቱ
ሁላችንም መጥፎ የድብርት ስሜት ውስጥ
ነበርን…ታኬ ላይ በደረሰው ነገር የሁላችንም
ልብ ተሰብራል…በጣምም ሀዘን ውስጥ
ወድቀናል፤ በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለን
የእሱ ምትክ የእሱ ማስረሻ አንተ ነህ ተብለህ
የሚለብሰውን ማልያ ሲሰጥህ መሸከም
የማትችለው ከባድ ኃላፊነት ስለሆነ በጣም
ያስፈራል ያስጨንቃል፡፡ ምክንያቱም ታከለ
በጣም ትልቅ ተጨዋች፣በጣም ከፍተኛ ቦታ
መድረስ የሚችል ልጅ ስለነበር ይሄንን አደራ
መሸከም ከባድ ነበር፡፡ ለእሱም ትልቅ ቦታ
ስላለኝ ይሄ ለእኔ አይገባም እኔ የእሱ ምትክ
የመሆን አቅም የለኝም ብዬ ነበር ያፈገፈጉት…
አሸናፊ በቀለ አሰልጣኝ አንተ ነህ ወይስ እኔ
ነኝ? ዝም ብለህ የምልህን ተቀበል ብሎ በቁጣ
ጭምር ሲጮሁብኝ የእሱን ትዕዛዝ ከመቀበል
ሌላ አማራጭ ስላልነበረኝ የዚህን ታላቅ
ተጨዋች ስም ለማስነሳት ምትክ ለመሆን
መጣር አለብኝ ብዬ ኃላፊነቱንም 7 ቁጥር
ማልያውያንም ተረክቤ ነበር፡፡
ሀትሪክ፡- …ታከለ አለማየሁ በእግር
ኳሱ በጣም እየተጠበቀ ባለበት ሰዓት በዚህ
መልኩ መለየቱን እንዴት ትገልፀዋለህ?
ሱራፌል፡- …ይሄንን ነገር ባስታውስኩ
ቁጥር በጣም ነው የማዝነው…በጣምም ነው
የምረበሸው፤ ክለቡንም ሀገሩንም መጥቀም
የሚችል ትልቅ ተጨዋች ነው እግር
ኳሱ ያጣው፡፡ እሱ ላይ በደረሰው ጉዳት
ሁላችንም በጣም ነው ያዝነው፤ያን ወቅት
ሁሉ ነገር አስጠልቶን ነበር…ጌታን ነው
የምልህ ከምነግርህ በላይ መጫወት ሁሉ
እስከሚያስጠላኝ ድረስ ነው ውስጤ በጣም
ተጎድቶ የነበረው። በዚያ ላይ የእሱ ምትክ
ማስረሻ አንተ ነህ ተብሎ አደራ ሲጣልብህ
በጣም ያስጨንቃል…ህይወት እንደዛን ጊዜ
አስጠልቶኝ፣ትርጉም ያጣሁበት ጊዜ የለም፡፡
ስፖርተኛ ስትሆን ከስራህ በኋላ ትዝናናለህ…
ትጫወታለህ፤ስትዝናና የሚያጋጥሙ ነገሮች
አሉ…እሱ ግን ባላሰበው ሁኔታ ለዚህ
መዳረጉ ነገሩን ትንሽ የከበደ ያደርገዋል፤ግን
ምን ታደርገዋለህ…የተፈቀደው ነው የሆነው፡
፡ በሰዓቱ ግን አልዋሽህም በጣም ተከፍተቼ
ሁሉም ነገር በጣም አስጠልቶኝ ነበር፤እንደ
አጋጣሚ ደግሞ በወቅቱ ፍቅረኛዬ…የአሁኗ
የትዳር አጋሬ የእሱ የአክስት ልጅ ነበረች…
በባለቤቴ የስጋ ዘመዴ የሆነበት አጋጣሚም
በመፈጠሩ እንደ አንድ ክለብ ተጫዋች ብቻ
ሳይሆን እንደ ሥጋ ዘመድ፣ እንደቤተሰቤ
ስሜቴን በጣም ጎድቶታል…የት ይደርሳል
የተባለ ልጅ በዚህ መልኩ መቅረቱ ሁሌም
ያማል፡፡
ሀትሪክ፡- … እስቲ ከዚህ መጥፎ ስሜት
እንውጣና ወደ ፋሲል ስላደረከው ዝውውር
እናንሳ….? ሱራፌል፡- …ሁላችሁም እንደምታውቁት
ፋሲል ከነማ የገባሁት ባለፈው አመት በ2ዐ11
ነው፤በእርግጥ በዚያን ወቅት አዳማ የመቆየት
ፍላጎቱም ነበረኝ…ፋሲሎች ግን የተሻለ ነገር
አቅርበው እነሱ ጋር መጥቼ እንድጫወት
በጣም አግባቡኝ፡፡ ያው የምትሰራው
ለመለወጥ ቢሆንም ራሴንም ሌላ ከለብ፣
ሌላ ደጋፊ፣ ሌላ ባህል ያለበት ክለብ ውስጥ
ገብቼ ራሴን ልፈትን ብዬ ጥያቄያቸውን
ተቀበልኩ፤ምክንያቱም አቅም አለኝ ብዬ
ስለማምን በአፍ ብቻ ሣይሆን በተግባርም
መፈተሽ ስለፈለኩ ወደዚያ አምርቻለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- …አሁን በፋሲል ከነማ
ሁለተኛ አመትህን ይዘሃል…በፋሲል ምን
አይነት የእግር ኳስ ህይወት እያሳለፍክ
ነው፤ በእርግጥም ራስህን ፈትነህ
አግኝተሃል…?
ሱራፌል፡- …በፋሲል እንዴት
እያሳለፍኩ እንደሆነ በግልፅ የሚታይ በመሆኑ
እኔ መናገር የሚጠበቅብኝ አይመስለኝም፤
ምክንያቱም ውጤቱ፣ ስኬቱ ራሱ አፍ አውጥቶ
ይናገራልና፡፡ በፋሲል እንደምታውቀው
የተለያዩ ትላልቅ ዋንጫዎችን ከጓደኞቼ ጋር
በማምጣት ለክለብም ለራሴም አዲስ ታሪክ
እያስፃፍኩ ነው፤የጥሎ ማለፍ፣ የአሸናፊዎች
አሸናፊ ዋንጫዎችን በማሳካት ወደ አዲስ
ታሪክ የተሸጋገርኩበት ክለብ ሆኖልኛል…
የሀገሪቱ ትልቁ ውድድር የሆነው የፕሪሚየር
ሊጉን ዋንጫም ለማንሣት እስከመጨረሻው
90 ደቂቃ ድረስ ተፋልመን ማሳካት ባንችልም
ይሄንን ታሪክ ለማፃፍም የተቃረብኩበት
ክለብም ነው፡፡ እኔ አሁንም የሊጉን ዋንጫ
ባናነሳም ጠንካራ ፉክክር እስከመጨረሻ
ያደረግንበት በመሆኑ አሁንም ዋንጫውን
ያገኘሁ ያህል ነው የሚሰማኝ፡፡ በአጠቃላይ
ግን በፋሲል በነበረኝ ቆይታ ሀገራዊ ጥሪ
ተደርጎልኝ ትልቅ ኃላፊነትም የተረከብኩበት
በመሆኑ ወርቃማ የሚል ቃል የሚገልፀው
ጥሩ ጊዜን እያሳለፍኩ ነው፡፡ ለቤተሰቦቼ፣
ለራሴ፣ ለክለቤና እንደ ሀገርም ትልቅ ታሪክ
ማፃፍ የጀመርኩበት ክለብ በመሆኑ በጣም
ደስተኛ ነኝ፡፡
ሀትሪክ፡- ገና ከመነሻው 2 ትላልቅ
ዋንጫዎችን፣ ሀገር የመወከል እድልን
በጠዋት አግኝተሃል፣ ይሄ የጠዋት ስኬት
ሱራፌልን ወዴት ይወስደዋል…?
ሱራፌል፡- …እኔ ገና እግር ኳስን
በአግባቡ ተጫውቼ አልጠገብኩም…ያም
ቢሆን ግን በዚህ አጭር ጊዜ ትላላቅ ክብሮችን
ማግኘቴ…የእነዚህ ታላላቅ ድሎች አካል
መሆኔ ነገ የተሻለ ደረጃ እንድደርስ ጥሩ ስንቅ
ይሆነኛል እንጂ አያኩራራኝም፣አያዘናጋኝም።
ፋሲል ከነማ የሀገሪቱ ክለቦች የበላይ፣ የሀገሬ
ብ/ቡድንም በአፍሪካ መድረክ ጎልቶ እንዲታይ
ለማደርገው ጥረት ትልቅ ጉልበትም የሚሰጠኝ
ነው የሚሆነው፡፡
ሀትሪክ፡- …ፋሲል ከነማ ባለፈው
አመት በኢንተርናሽናል የውድድር መድረክ
የመካፈል እድል ቢያገኝም ብዙ ርቀት
አልተጓዘም ከዚህ ምን ተማርክ…?
ሱራፌል፡- …ትክክል ነህ ብዙ
ርቀት አልተጓዘም… ነገር ግን ብዙ ርቀት
ባንጓዝም በጣም ብዙ ትምህር አግኝተን
በታል፤በኢንተርናሽናል ጨዋታ ራሳችንን
የምንለካበት እድልን ፈጥሮልን ያለፈ
በመሆኑ ተምረንበታል፡፡ የሀገሬ ክለብም እንደ
ክለብ…እኔም እንደ ተጨዋች በግል የት?
ነው ያለነው? የሌለሎች ሀገሮች ክለቦችስ?
አፍሪካዊያን ተጫዋቾችስ? የሚለውን በተግባር
የመፈተሽ፣ የማየት እድል ሰጥቶን ያለፈ
በመሆኑ ብዙ ርቀት ባንጓዝም የምንማርበትን
እድል ፈጥሮ ስላለፈ እንደ መልካም
እድልም ነው ያየሁት፡፡ በጣም የሚገርምህ
ሌላ ያየሁበት ነገር እንደ ግልም እንደ
ክለብም ኢትዮጵያዊያን ኳስ እንደምንችል
ያየሁበትም ነው… በራሳችን ስለማናምን…
ራሳችንን ዝቅ ስለምናደርግ እንጂ እኛ ኳስ
እንደምንችል እንደምንበልጣቸው በደንብ
ያየሁበት መድረክም ነበር፡፡ እነሱ አውሮፓም
ይሁን የትም ሄደው ይጫወቱ… ጉልበት
ይበልጡናል… እሱን እናምናለን፤ እኛ ግን
ኳሱን እንደምንችል በደንብ አይቼበታለሁ…
ተምረንበታልም፡፡
ሀትሪክ፡- …ባለፈው የውድድር
ዘመን ፋሲል እስከጨረሻው ደቂቃ
ተፋልሞ ለጥቂት የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ
አጥቷል፤ዘንድሮስ ያጣችሁትን የሊጉን
ዋንጫ የምታሳኩበት አመት ይሆናል ብለህ
ታምናለህ?
ሱራፌል፡- …በግሌ በጣም ነው የማም
ነው… የተዘጋጀነውም የምንጫወተውም
ይሄንን ለማሳካት ነው፤ ይሄን ስልህ ግን
በመመኘት ብቻ ስለማይመጣ ያንን ለማሳካት
ጠንክረን እንሠራለን ውጤታማ ለመሆንም
እንጥራለን፡፡ ባለፈው እንድናጣ ባደረገን ነገር
ላይ በመስራት ለማሳካት ነው እየተዘጋጀን
ያለነው፤አሁን በአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ
አቅማችን የት ጋ እንዳለ ለማሳየት ሞክረናል…
ማደግ የሚችል ጠንካራ ቡድን ነው ያለን…
ጠንክረን ከሠራን ምኞታችንን ወደ እውነትነት
መቀየር ይቻላል፡፡
ሀትሪክ፡- …የፋሲል ከነማ ደጋፊዎ
ችን ግለፅልኝ ብልህ እንዴት ነውየ
ምትገልፃቸው…?
ሱራፌል፡- …የፋሲልን ደጋፊ እንዴት
ብዬ እንደምገልፅልህ አላውቅም…ይሄ
ያልኩበት ምክንያት እነሱን በትክክል የሚገልፅ
ቃል ስለማላገኝ ነው፡፡ የፋሲል ከነማ ደጋፊ
ክለቡን ከልቡ የሚወድ የሚደግፍ እውነተኛ
ደጋፊ ነው፡፡ ድጋፋቸው በሜዳችን ብቻ
የተገደበ አይደለም…አብሮህ እየተንከራተተ
ፀሐይና ብርድ እየመታው የሚደግፍ ሪሱን
አሳልፎ ለቡድኑ የሚሰጥ ደጋፊ ነው፡፡
ደጋፊውን የተለየ የሚያደርገው ሌላው ትልቁ
ነገር ስታሸንፍ የሚከብህ የሚጨፍር ስትሸፍ
ከአጠገብህ የሚጠፋ ደጋፊ አለመሆኑ ነው፡፡
እግር ኳስ ነውና አንዳንዴ አቋምህ ሲወርድ
ስትሸነፍ ደጋፊው ጀርባ አይሰጥህም፤ስትሸነፍ
አይዞህ ብሎ የሚያበረታታ ምርጥ ደጋፊ
በመሆኑ ከልቤ ነው የምወዳቸው በጣምም
ነው የማከብራቸው፡፡
ሀትሪክ፡- …የአማካይ ተጨዋች ነህ…
አንተ በምትጫወትበት ቦታ አንድ ተጫዋች
ብቻ ጥራ ብልህ ማንን ትጠራለህ?
ሱራፊል፡- …ይሄ ምን ያጠያይቃል…?…
ዳዊት እስጢፋኖስን ነዋ የምልህ…!…ከእሱ
ውጪ መጥራት ይቸግረኛል…?
ሀትሪክ፡- …ከሀገር ውስጥ የሱሬ
ምርጡ አሰልጣን ማነው ብልህስ…መልስህ
ምንድነው የሚሆነው…?
ሱራፊል፡- …ምንም አልዋሸህም…ለእኔ
ምርጡ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ነው፡፡
ሀትሪክ፡- …ሱራፌል አሁን የብቃቱ
ጫፍ ላይ ደርሷል…?…
ሱራፊል፡- …ኧረ በፍፁም…!…
ገና ይቀረኛል…!…ገና መጫወት
ጀመርኩ ብዬ ነው የማስበው እና ብዙ
የምሰራቸው የሚቀሩኝ ስራዎች አሉ፤ሌላው
እንዲታወቅልኝ የምፈልገው ሱራፊል የብቃቱ
ጫፍ ላይ ነው ብዬ የምኩራራ ራሴን
የምቆልል ሳይሆን ገና ለሀገሬም ለክለቤም
ብዙ መስራት የሚጠበቅብኝ ብዙ የሚቀረኝ
ተጨዋች እንደሆንኩ ነው ፡፡
ሀትሪክ፡- …ግብ ማስቆጠር ወይስ
ለግብ የሚሆን ያለቀለት ኳስ ማቀበል…?…
የቱ ያስደስትሃል…?
ሱራፊል፡- … (ሣቅ)…ማስቆጠርም
ያስደስተኛል፤ ግን ከዚህ ይልቅ ያለቀለት
ኳስ ጨርሼ አቀብዬ የቡድን ጓደኞቼ ግብ
ቢያስቆጥሩ ደግሞ የበለጠ ያስደስተኛል፡፡
ሀትሪክ፡- …የጨረሱ ለጎል የሚሆን
ኳስ ከማቀበል ባለፈ ቅጣት ምትም ከርቀት
መትቶ የማስቆጠር ኳሊቲም ባለቤት
ነህ፤ይሄንን እንዴት አዳበርከው…?…
የምትሰራው የተለየ ልምምድስ አለ…?
ሱራፊል፡- …ሁሌም አንድ ልምድ
አለኝ…ትሬይኒንግ ከመጀመራችን በፊት
ሰውነቴን ካሟሟኩ በኋላም ይሁን
ትሬይኒንግ ስንጨርስም በበረኛም፣ በረኛ
በሌለበትም ከርቀት የመምታት የዘወትር
ልምድ አለኝ፤ከርቀት ጠንከር ያለ ሹት
በመምታት የመሞከር የብዙ ጊዜ ልምድ
አለኝ፤ይሄንን ደጋግሜ ማድረጌ በዚህ በኩል
ያገዘኝ ይመስለኛል፡፡ ከዚህ ውጪም በአለም
እግር ኳስ የቅጣት ምት ኤክስፐርት የሚባሉ
ተጨዋቾች እንዴት እንደሚለማመዱ፣
እንዴት ግብ እንደሚያስቆጥሩ በቪዲዮ
ጭምር እከታተላለሁ፤ምናልባት የዚህ ድምር
ውጤት የጠቀመኝ ይመስለኛል፡፡
ሀትሪክ፡- በፕሪሚየር ሊግ ከየትኛው
ቡድን ጋር ስትጫወት ይመቸሃል…?
ሱራፊል፡- …ከኢት.ቡናና ከቅ/
ጊዮርጊስ ጋር ነዋ…!… (ሳቅ)…ከእነሱ
ጋር ስትጫወት ጨዋታው አንድ ጨዋታ
ብቻ አይመስልም፤የሜዳው ድባብ፣ የደጋ
ፊው አደጋገፍ የመጫወት ስሜትን የሚያቀ
ጣጥል፣የሆነ ነገር እንድትሰራ የሚያነሳሳ
ነው፡፡
ሀትሪክ፡- …ማን አጠገብህ ሆኖ
ሲጫወት ይግባባሃል… ጨዋታህንም
ያቀልልሃል…?
ሱራፊል፡- …እ…!… ስኪመር ላይ ብሩክ
ቃልቦሬ ከጎኔ ሲሆን ጨዋታ ያቀልልኛል…
ምን እንደማደርግም ቀደሞ ስለሚያውቅ
በጣም ይመቸኛል፡፡
ሀትሪክ፡- … አንተ በምትጫወትበት
አማካይ ቦታ በተቃራኒ ሆኖ የሚያስቸ
ግርህ… አላነቃንቅ ብሎ የሚፈታተንህ
ተጨዋችስ?
ሱራፊል፡- … አልዋሽህም… በዚህ ደረጃ
ገጠመኝ የምለው ተጨዋች የለም…
ሀትሪክ፡- … አብሮኝ ቢጫወት ወይም
አብሮኝ ባለመጫወቱ ብለህ የምትቆጭበት
ተጨዋችስ…?
ሱራፊል፡- … በሁለቱም መንገድ ዳዊት
እስጢፋኖስ… በጣም አያደነኩትነው ያደኩት…
በአጨዋቱም በጣም ነው የምወደው… ፡፡
ሀትሪክ፡- … ከሰዎች ባህሪ ባላየው…
ባልሰማው የምትለው…?
ሱራፊል፡- … ራስ ወዳድ የሆነ ሰው
አይመቸኝም…፡፡
ሀትሪክ፡- …ከውጪ ክለቦች ድጋፉህን
ያለስስት የምትሰጠው?
ሱራፊል፡- … ለአርሴናል…
ሀትሪክ፡- … የምታደንቀው
ተጨዋችስ…?
ሱራፊል፡- ሁለት ናቸው ኔይማርና
ሊዮኔል ሜሲ፡፡
ሀትሪክ፡- የEBCየአመቱ ምርጥ
ተጫዋች ሽልማትን አማኑኤል ገ/ሚካኤል
አሸንፏል፤ አሸንፋለሁ ብለህ ነበር… ?
ሱራፌል፡- …እውነቱን ንገረኝ ካልከኝ
አዎን…በሚገባ አሽንፋለሁ ብዬ ራሴን በደብ
አሳምኜ እርግጠኛ ሆኜ ነበር የመጣሁት…
ግን የሚያሸንፈው አንድ ሰው ብቻ ነበርና
አማኑኤል አሸናፊ ሆኗል፤ አማኑኤል አሸናፊ
የሆነው በአጋጣሚ ወይም በቀልድ ሳይሆን
ጠንክሮ ስለሠራ ስለሆነ በዚህ አጋጣሚ
እንኳን ደስ አለህ ልለው እፈልጋሁ…እኔም
በቀጣይ ጠንክሬ በመስራት የዚህ እድል
ባለቤት ለመሆን እጥራለሁ…፤… እዚህ ላይ
ግን አንድ ቅር ያለኝን አስተያየት ብሰጥ ደስ
ይለኛል …
ሀትሪክ፡- …ምንድነው ቅሬታህ
ቀጥል…?
ሱራፌል፡- በመጀመሪያ EBC ይሄን
ሽልማት በማዘጋጀቱ ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡
…ግን ልብ ሳይሉት ቀርተው ይሁን ምክንያቱ
ምን እንደሆነ ባላውቅም ሽልማት ያዘጋጁት
አንደኛ ለወጣው ብቻ ነው… አምናም
የነበረው ይሄው ነበር፤በእኔ የግል አመለካከት
ይሄ ትክክል ነው ብዬ አላምንም፡፡ መቼም
የውጪው ተሞክሮ ነው ወደ ሀገር ቤት
አምጥተን ነው የምንሰራው፤ ፊፋም ሆነ ካፍ
የኮኮብ ምርጫን ሲያካሄዱ ከ1-3 ያሉትን ነው
የሚሸልሙት፡፡ የገንዘቡ ወይም የሽልማቱ
መጠን ይለያይ እንጂ ከ1-3 የወጡት
ይሸለማሉ፡፡ አሁን በ EBC ሽልማት ግን
ይሄን አላየሁም፡፡ እኔ አሁን እስከ መጨረሻ
ነበርኩበት ግን ከሽልማቱ ስወጣ ሁለተኛም
ልሁን ሶስተኛም ወደፊት ለልጆቼ ማውራት
ብፈልግ ማስረጃ የለኝም፡፡ ሌላ ቢቀር
እንኳን መታጨታችንንና የወጣንበትን ደረጃ
የሚገልፅ ለታሪክ በማስታወሻነት የሚቀመጥ
ትንሽ ሰርተፊኬት ወይም ዋንጫ ነገር ቢኖር
መልካም ነበር…ይሄ ባለመሆኑ ቅር ብሎኝ
ነው የወጣሁት፡፡ እኔ ለሽልማቱ ክብር ሰጥቼ
ፕሮቶኮል ጠብቄ ከመቐለ ብ/ቡድን ጥዬ
መጥቼ ነው በቦታው የተገኘሁት…ከሽልማቱ
በኋላ አንድም ማስታወሻ ባለመኖሩ በጣም
አዝኜ ተበሳጭቼ ለምን መጣሁ? እስከማለት
ሁሉ ደርሼ ነው የወጣሁት፤ ማስታወሻ ትንሽ
ሰርተፍኬት ነገር እንኳን እንዴት አይዘጋጅም?
እንዲህ ከሆነ መታጨት እስከመጨረሻው
መድረስስ ትርጉም ምንድነው? ትንሽ ይሄ
አላስደሰተኝምና በቀጣይ ቢያስቡበት፡፡
ሀትሪክ፡- …በቀጣይ ሣምንት
ፌዴሬሽኑ ዘግይቶም ቢሆን የ2011 ኮኮብ
ተጨዋቾችን ያሳውቃል… የዚህ ሽልማት
ባለቤት ማን ይሆናል…ሱራፌል ወይስ
ሌላ…?…
ሱራፌል፡- …ይሄንን የሚያውቁት
እነሱ ናቸው…እንደ እኔ ግን የጥሎ ማለፍ፣
የአሽናፊዎች አሸናፊ ዋንጫን፣ ክለቤን
ለአፍሪካ የክለቦች ሻምፒዮና ያበቃሁ፣ሀገሬን
የማገልገል እድል ያገኘሁበት አመትን
ስላሳለፍኩ እነዚህ ስኬቶቼ ለዚህ ክብር
ያንሳሉ ብዬ አላስብም፤ እንግዲህ የሚሆነውን
መጠበቅ ነው፡፡
ሀትሪክ፡- …ሱሬ እኔ ጨረስኩ ጊዜህን
ፈቅደህ አንባቢዎቼንም እኔንም አክብረህ
ለቃለ-ምልልሱ ስለተባበርከኝ አመሰግኜህ
ከመለያየታችን በፊት የረሳሁት፣ቀረ
የምትለው ነገር ካለ መድረኩን ልልቀቅ
ልህ…?
ሱራፌል፡- …በመጨረሻ በእኔ እድገት
ላይ አሻራቸውን ያሳረፉትን ማመስገን ነው
የምፈልገው… በዚህ በኩል በመጀመሪያ
ቅድሚያ የምሰጠው ለፈጠረኝ አምላክ ነው…
መከራዋን አይታ ለዚህ ስኬት ያበቃችኝ እናቴ
ምስጋና በትልቁ ይገባታልና እናቴን ሮማን
እሸቴን (ብሩክታይትን) አመሰግናታለሁ፤ ብዙ
ጊዜ ልጅ ስትሆን እናትህ የምትልህን ትሰማለህ
ትፈፅማለህ…የእኔ እናት ግን ፍላጎቴን
በማክበር እኔ የምለውን እየሠማች፣እየደገፈች
ትጥቅ ሁሉ ከሌላት ገንዘብ ላይ እየገዛች
እየላከችልኝ፣ እያበረታታችኝ ነው ለዚህ
ያደረሰችኝና አባትም እናትም ሆና ያሳደገችኝ
እናቴን በዚህ አጋጣሚ አመሰግናለሁ፡፡ ከእሷ
ሌላ የእናቴ ያህል ሆና ያሳደገችኝ አያት
ሽዋዬ እሸቴንም እንደዚሁ አመሰግናለሁ…
እግዚአብሔር ይስጥልኝ እላለሁ፡፡ ከቤተሰቦቼ
ሌላ ያለኝን ነገር በማየት ትልቅ ደረጃ
እንድምደርስ ቀደሞ በመገመት ለለፉብኝ
አሰልጣኞቼ ሱልጣን መሀመድና ኃይሌ
ካሱ ለውለታቸው እያመሰገንኩ በህይወቴ
ለእነሱ ትልቅ ቦታ እንዳለኝ በዚህ አጋጣሚ
እግዚአብሔር ይስጥልኝ ማለትም እፈልጋለሁ፡
፡ ሌላው ሳልናገር ማለፍ የማልፈለገው በጣም
የምታስብልኝ፣ በሙያዬ ስኬታማ እንድሆን
የምትደግፈኝን ባለቤቴን ሜሮን ሰለሞንን
ለድጋፋዋ ከልቤ አመሰግናለሁ፡፡ ክለቤንም
ሀገሬንም የበለጠ እንዳገለግል ለምታደርግልኝ
ሁሉ በዚህ አጋጣሚ ላመሰግንሽ እወዳለሁ
በልልኝ፡፡ የሀትሪክ ዝግጅት ክፍልንም አተንም
ለሰለጠኸኝ እድል እንዲሁ ምስጋናዬ የበዛ
ነው፡