በተጠናቀቀው የኢትዮጵያ ፕሪሜየርሊግ ሁለተኛው ዙር ላይ መቐለን የተቀላቀለው ጋቶች ወደ ግብፅ ሊግ ኣዲስ ያደገውን ኤልዱናን በሁለት ዓመት ውል ተቀላቅሏል።ለመቐለ 11 ጨዋታዎችን መጫወት የቻለው ጋቶች 2 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።
ባለፈው ኣመት ሌላው የግብፅ ክለብ ዋዲ ደግላ እና ቢድ ቨስት ዊትስ ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሶ የነበረው ጋቶች ኤልዱናን መቀላቀሉን ተከትሎ በቀጣይ ዓመት ግብፅ ፕሪሜየርሊግ ሥስት ኢትዮጵያውያን ምንመለከት ይሆናል፤እንደሚታወቀው ሽመልስ ለፔትሮጀት ዑመድ ኡኩሪ ለሶምሃ እየተጫወቱ ይገኛሉ።