በ29ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ እሁድ እለት መደረግ የነበረበት የሊግ ጨዋታ በጥሎ ማለፍ ጨዋታ ምክኒየት ዛሬ 10:30 ላይ ደደቢት ከ ሲዳማ ቡና ጨዋታ ተካሂዷል፡፡ በጨዋታውም ደደቢቶች በሁለተኛው አጋማሽ መጠናቀቂያ ላይ በኘሪሜየር ሊጉ ታሪክ በ1993 በዮርዳኖስ አባይ በ24 ጎል የተያዘውን ሪከርድ ለመስበር የተጠጋበትን ጎል በ81 ኛው ደቂቃ ላይ ጌታነህ ከበደ አስቆጥሯል፡፡በዚህም በአመቱ ያስቆጠራቸው የከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ደረጃውን ወደ 23 ሊያሳድግ ችሏል፡፡
ጌታነህ ከበደ በ1993 በዮርዳኖስ አባይ የተያዘውን ሪከርድ ለመጋርት ወይም ለመስበር አንድ እና ከዚያ በላይ ጎሎች ማስቆጠር ይጠበቅበታል፡፡ በዚህም የ30ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ ጨዋታ ወደ ወላይታ አምርቶ የወራጅ ስጋት ካለበት ወላይታ ድቻ ጋር የለበትን ጨዋታ መጠበቅ ግድይለዋል፡፡