በክረምቱ ዝውውር መስኮት በንቃት እየተሳተፋ ሚገኙት ኣጼዎቹ ኣምና በኣጥቂ ክፍል የታየባቸውን ክፍተት ለመቅረፍ ናይጀርያዊ ኣጥቂ ኢዙ ቦቦ ኣዙካን በሁለት ዓመት ውል ማስፈረም ችሏል።
ከ2008-2018 ለ 14 ክለቦች መፈረም የቻለው ኣዙካ ለሳንሻይን ስታርስ(ናይጀርያ)፣ኣል ኢትሃድ ትሪፖሊ(ሊብያ)፣ኣርትይሽ ፓልቮዳር(ካዛኪስታን)፣ዬኒ ማላትያስፖር(ቱርኪ) መጫወት ችሏል።ከ2012 በኃላ በክለብ ደረጃ 95 ጨዋታዎችን ያካሄደ ሲሆን 19 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።ኣዙካ ለመጨረሻ ጊዜ የተጫወትበት ክለብ በህንድ ሊግ ለሚሳተፈው ጃምሸድፑር ሲሆን 4 ጨዋታዎች ላይ መጫወት ችሏል።
በብሄራዊ ቡድን ደረጃም ከ23 ዓመት በታች ናይጀርያ ብሄራዊ ቡድን 4 ጨዋታዎች ኣድርጎ ሁለት ግብ ማስቆጠር ችሏል። በክረምቱ 10 ተጨዋቾችን ያስፈረሙት ፋሲሎች በ2011 የኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ ለዋንጫ ሊፎካከሩ እንደሚችሉ ይገመታል።