የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሊግ ኮሚቴ ፋሲል ከነማ ከወላይታ ድቻ በ11ኛ ሳምንት የፊታችን ጥር 11 ቀን ከቀኑ በ ዘጠኝ ሠዓት በፋሲለደስ ስታዲየም እንዲጫወቱ ፕሮግራም ማውጣቱ ይታወሳል ይህንን ተከትሎ የፋሲል ከነማ ቡድን የዕለቱን ጨዋታ በተጠቀሰው ቀን ለማድረግ እንደሚቸገርና ጨዋታው ወደ ሌላ ቀን እንዲዛወር በቀን 03/05/11 ለፌዴሬሽኑ በተፃፈ ደብዳቤ ጥያቄ አቅርቧል።
ፋሲል ከነማ ጨዋታው እንዲዛወርለት ፌዴሬሽኑን የጠየቀበትን ምክንያት በደብዳቤው ላይ እንዳስቀመጠው ከወላይታ ድቻ ጋር ጨዋታው በሚካሄድበት ጥር 11 ቀን በጎንደር የጥምቀት በዓል የሚከበርበት ታላቅ ቀን በመሆኑ የፀጥታ አስከባሪም ሁለት ቦታ ለመመደብ አስቸጋሪ በመሆኑ እንዲሁም የጥምቀት በዓልን በተንቀሳቃሽ ቅርስነት ለመመዝገብ የዩኔስኮ ከፍተኛ ባለሙያዎችና ቱሪስቶች ዲፕሎማቶች በብዛት የሚመጡበት ቀን በመሆኑ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ጨዋታ ማካሄድ አስቸጋሪ ሰለሆነ ጨዋታው ይተላለፍልን ሲል በደብዳቤ ጠይቋል።ፌዴሬሽኑ ለፋሲል ከነማ ጥያቄ እስከ አሁን ድምፁን ባያሰማም ጥያቄው አሳማኝ በመሆኑ የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ወደ ተስተካካይ ጨዋታ ጎራ መግባቱ አይቀሬ መሆኑን ስማችን አይገለፅ ያሉ የፌዴሬሽኑ ሠዎች በተለይ ለhatricksport.com ገልፀዋል።
ፋሲል ከነማ ከወላይታ ድቻ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ እንዲተላለፍ ጥያቄ አቀረበ
Hat-trick Weekly Sport Newspaper Founder & Managing Editor.
The First Color Sport Newspaper in the country.