የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ የሆነው ፋሲል ከነማ ጋብርኤል አህመድ በአንድ ዓመት ውል አስፈርሟል።
ስዩም ከበደን በአሰልጣኝነት ከቀጠረ በኃላ በተጨዋቾች ዝውውር ላይ ዝምታን መርጠው የነበሩት አፄዎቹ ጋናዊውን አማካይ ጋብርኤል አህመድን(ጅብሪል) ማስፈረም ችለዋል።
ከመቐለ 70 አንደርታ ጋር የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮን መሆን የቻለው የቀድሞው የደደቢት፣ኢትዮጵያ ንግድባንክ፣ሃዋሳ ከተማ እና መቐለ 70 እንደርታ አማካይ ጅብሪል ፍፁም አለሙ ያጣውን የፋሲል ከነማ መሃል ክፍልን ሊያጠናክር አንደሚችል ይገመታል።