የእርስበርሳችን አለመስማማትና አለመግባባት ለሀገር ቅድሚያ አለመስጠት ችግራችን በስዊዘርላንድ ዙሪክ አደባባይ የፊፋን በር ማንኳኳት መጀመሩ በርካቶቻችሁን ያስጨነቃችሁ ጉዳይ ዛሬስ መፍትሄ ያገኝ ይሆን ???
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የፕሬዚዳንት እና የስራ አስፈፃሚ ምርጫ ለአራት ጊዜ መራዘሙን ተከትሎ ጉዳዩን ለማጣራት የአለም አቀፉ እግር ኳስ አስተዳዳሪ (ፊፋ) ተወካይ አካላት ዛሬ አዲስ አበባ መግባታቸውንና እነዚህ መልዕክተኞች በጁፒተር ሆቴል ከ 5ቱ ዕጬ ፕሬዝዳንቶች ከ9 አስመራጭ እና ከ3 ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ እንዲሁም ጊዜያዊ ዋና ፀሐፊው አቶ ሰለሞን ገ/ስላሴ ጋር በጁፒተር ሆቴል ጥልቅ ውይይት እንደሚያደርጉ የተነገረ ቢሆንም የስብሰባ ቦታው ከተባለው ሆቴል ወደ ሂልተን ዙሯል፡፡
ጥቅምት 30/2010 ዓ,ም ተብሎ እስከ የካቲት 24/2010 ዓ,ም ድረስ ለስድስት ወራት ያልተካሄደው ፕሬዝዳንታዊና ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ምርጫ አሁንም አነጋጋሪነቱ ቀጥሏል፡፡ፊፋ የመጨረሻውን ቀን ለመወሰን የላካቸው መልዕክተኞች ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ ከቀኑ
9፡30 በሂልተን ሆቴል ከማናጅመንት አባላት ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን ከሰዓታት በኋላ የአስመራጭ ኮሚቴና ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ አባላትን ማነጋገራቸውም ታውቋል፡፡
የፊፋ ተወካዮች አሁን በሂልተን ሆቴል አምስቱን ዕጩ ፕሬዝዳንቶች አቶ ጁነዲ ባሻን ጨምሮ እንዲሁም ዋና ፀሐፊውን አቶ ሰለሞን ገ/ስላሴን ያካተተ ሰፋ ያለ ውይይት በማድረግ ላይ ሲሆኑ መልዕክተኞቹ የአስመራጭ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወደ ሆኑት አቶ ዘሪሁን መኮንን ላይ ጣታቸውን በመቀሰር ፡ ምሺቱን ባለድርሻ አካላትን በቡድንና በነጥብ እያነጋገሩ ወደ መፍትሄው በር እየተጓዙ ይመስላሉ፡፡
- ማሰታውቂያ -
ውሳኔ ከተወሰነና ዕጩዎች ከታወቁ በኋላ ህግ በድምጽ አይሻርም ከተባለ እዚያው መቆም ነበረበት እንጂ ከተወሰነ በኋላ ለፊፋ ደብዳቤ መጻፍ አልነበረበትም በሚል መልዕክተኞቹ ተቃውመዋል።
የአስመራጭ ኮሚቴው አባላትም አቶ ዘሪሁን የላኩት ደብዳቤ ከኮሚቴው ዕውቅና ውጪ በራሳቸው ፍላጎት ብቻ ደብዳቤውን ወደ ዙሪክ መላካቸውን ለመልዕክተኞቹ
አጋልጠዋል።
የፊፋ መልዕክተኞች ከፕሬዝዳንታዊው ዕጩዎች መካከል አቶ ተካ አስፋውን ቀደም ብለው ከደቂቃዎች በፊት በግል ያነጋገሩ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ሌላኛውን እጩ ፕሬዝዳንት ዶክተር አሸብርን በማነጋገር ላይ ናቸው።
በአሁኑ ሰዓት የፊፋ መልዕክቶች ከሚመለከታቸው የፌዴሬሽኑ አካላት ጋር በሂልተን ሆቴል የሚያደርጉትን አነጋጋሪና መፍትሄ አፈላላጊ ውይይቶች ተጨማሪ መረጃዎችን ይጠብቁን፡፡