በያዝነው ዓመት አጋማሽ ከወልዲያ ከተማ ጋር በተለያዩ ምክኒያቶች ባለመስማማቱ ከክለቡ ጋር መቀጠል ያልቻለው ፍፁም ገብረማርያም በመጨረሻ ሰዓት ማረፊያው መከላከያ መሆኑ ተረጋግጧል።
ጦሩ በሊጉ ሁለተኛው ዙር ከውጤት ቀውስ ጋር በተያያዘ አሰልጣኙን በማሰናበት አሰልጣኝ ስዩም ከበደን መቅጠሩን ተከትሎ አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም ላይ ይገኛል።
በአጥቂ ስፍራ ላይ ስማቸው ከሚጠቀሱት መካከል ፍፁም ገብረማርያምን በዛሬው አለት ማስፈረም ችሏል።
ተጫዋቹ ከዚህ ቀደም ለሙገር ሲሚንቶ ፣ለቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ለኤሌክትሪክና ለወልዲያ ከተማ መጫወት እሚታወቅ ነው።