የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ 7ኛ ሳምንት ቀሪ 1መርሃ ግብር ያከናወኑት ጅማ አባጅፋሮች ሁለተኛ ድላቸውን ኢትዮጵያ ቡናን 2-0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል፡፡
09:02 ሲል የጀመረው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በጅማ አባጅፋር በኩል በ4-3-3 አሰላለፍ እንዲሁም በኢትዮጵያ ቡና በኩል 4-2-2 አሰላለፍ ሲቀርቡ በሙሉ የጨዋታ ሰዓት በኳስ ቁጥጥሩ የበላይ የነበሩት ኢ/ቡናዎች ነበሩ፡፡
ነገር ግን ወደ ግብ በመድረሱ ረገድ የተዋጣላቸው ባለሜዳው ጅማ አባጅፋር ነበር 22ኛው ደቂቃ ላይ ከማዕዘን ምት ተመስገን ገ/ኪዳን ያሻማትን ኳስ ናይጄሪያዊው አጥቂ ኦኪኪ አፎላቢ ወደ ግብነት ቀይሯት ጅማዎችን ቀዳሚ አድርጎል፡፡
ኢትዮጵያ ቡናዎች በአንፃሩ ሳምሶን ጥላሁን ኤልያስ ማሞ እና አስራት ቱንጆ ተደጋጋሚ የማግባት አጋጣሚን ቢያገኙም ማስቆጠር አልቻሉም፡፡ በአንፃሩ 44ኛ ደቂቃ ላይ ተመስገን ገ/ፃዲቅ የኢትዮጵያ ቡናን ተከላካዮች መዘናጋት ተጠቅሞ 2ተኛ ግብ አስቆጥሮ ጅማ አባጅፋር 2-0 በሆነ ውጤት እየመራ የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቋል፡፡ በሁለተኛው አጋማሽ ቡናዎች ቶማስ ስምረቱን በጉዳት አጥተው መግባታቸው የተወሰነ የመከላከል አቅማቸውን ቢያሳጣቸውም በአማካያቸው እያሱ ታምሩ መልካም እንቅስቃሴን ማድረግ ችለዋል፡፡ እጅግ ሀይል የተቀላቀለበት እንቅስቃሴን በሁለቱም ክለቦች የተስተዋለ ሲሆን የእለቱ ዳኛ ዝምታን መምረጣቸው ከደጋፊዋች ዘንድ ተቃውሞን አስተናግደዋል፡፡
- ማሰታውቂያ -
ኢትዮጵያ ቡና ጫና ፈጥረው ቢጫወቱም ግብ ማስቆጠር ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡ በርካታ የሁለቱም ክለቦች ደጋፊዎች በታደሙበት ጨዋታ የኢትዮጵያ ቡናው አዲሱ አሰልጣኝ ዲዲዬ ጎሜዝም ከተመልካቹች ጋር ጨዋታውን ተመልክተዋል ፡፡
አሰልጣኝ ሀብተወልድ ደስታ ላይ በአጨዋወታቸው ደስተኛ ካለሁኑት የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎቹ ተቃውሞ ደርሶባቸዋል፡፡ይሁንና ጨወታው ጅማ አባጅፋር በመጀመሪያው አጋማሽ ባስቆጠሩት ግብ 2-0 አሸናፊ በመሆን ወደ ድል ተመልሰዋል፡፡
የአሰልጣኞች አስተያየት
ገብረ-መድህን ሀይሌ- ጅማ አባጅፋር
“ዛሬ እኛ በጨዋታው በቁርጠኝነት ጨዋታውን እንድናሸንፍ ወደ ሜዳ የገባነው ማ ተጫዋቾቹም ያንን አድርገዋል፡፡
በመጀመሪያው አጋማሽም ጫዋታውን ገለናል ማለት እችላለው በተደጋጋሚ ነጥብ መጣላችን ከስነልቦና አንፃር ጎድቶን ነበር፡፡ ማሸነፋችን ያነቃቃናል ማለት እችላለው ፡፡ የሊጉ መርሀ ግብር አወጣጥ ግን ወጥ ያልሆነ ነው በቀጣይ ሶስት ተከታታይ ጫወታ ነው ያለን የእሁድ ጨዋታ ዛሬ መምጣቱ ግራ ያጋባኛል፡፡”
የኢትዮጵያ ቡናው አሰልጣኝ ሀብተወልድ ለድህረ ጨዋታ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡
[team_standings id=”6559″ title=”” number=”16″ columns=”p,gd,pts” show_team_logo=”1″ show_full_table_link=”0″ align=”none”]