ሳምንታዊ ባለቀለም የስፖርት ጋዜጣ የሆነችው ተወዳጇ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ እንደተለመደው ሁሉ ነገም ማክሰኞ ታህሳስ 24/2010 ዓ.ም በማለዳው በእጅዎ ልትገባ መሰናዶዋን አጠናቅቃለች፡፡
ለመሆኑ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ይሆን?
-ከሀገር ውስጥ፡- በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 9ኛ ሳምንት ደደቢት 1-0 ኢትዮጵያ ቡና ባሸነፈበት ጨዋታ ከኢትዮጵያ ቡና በኩል ጥሩ እንቅስቃሴን ያሳየው እያሱ ታምሩ ስለ ኢትዮጵያ ቡና ወቅታዊ አቋም እሚለው ነገር ይኖራል፡፡ ቅዱስጊዮርጊስከ መከላከያ አቻ በተለያዩበት ጨወታ መልካም እንቅስቃሴን ማድረግ የቻለው አብዱልከሪም መሀመድ ስለ ፈረሰኞቹ አቋምና ስለራሱ ወቅታዊ ብቃት ከሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ጋር ጣፋጭ ቆይታን አድርጓል።
ከባህር ማዶ፡- ከእንግሊዝ ዳኞች ጋር እሰጣገባ ውስጥ የገቡት የአርሰናሉ አለቃ አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር የእንግሊዝ ዳኞች ኘሮፌሽናል አይደሉም በማለት የተናገሩትን ሙሉ ቃለምልልስ አካተናል፡፡
ግብፅዊው መሀመድ ሳላህ በየርገን ክሎፕ ቡድን ውስጥ አስደናቂ ብቃቱን አየሰጠ ስለ ሚገኘው አገለግሎት በሰፋት ተዳሷል፡፡
- ማሰታውቂያ -
በኦልዲስ በት ጉዲስ አምዳችን ደግሞ ለሁለቱም ታላላቅ ቡድኖች ኢት.ንግድ ባንክ ና በኢት.ቡና የተጫወተው መሀሪ አላምረው ጋር ሰፋ ያለ ቆይታ አድርገናል።
እናም ሌሎች ያልተሰሙ አዳዲስና ትኩስ ዘገባዎችን ነገ ማለዳ ይዛ እጅዎ ትገባለች፡፡
በርካታ አንባቢዎቻችን ባቀረባችሁልን ተደጋጋሚ ጥያቄ መሰረት ሀትሪክን በሳምንት ሁለት ቀን በቅርቡ ይዘን እንቀርባለንና ጠብቁን፡፡ ተጨማሪና ትኩስ መረጃዎችን በርካታ ተከታታዮች ባሉት hatricksport.com ድረ-ገፃችን ይጎብኙን፡፡
ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡
መልካም ንባብ