በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 7ኛ ሳምንት ጨዋታ ለገጣፎ ከተማን ያስተናገደው ሽረ እንዳስላሴ 1-1 በሆነ ውጤት ነጥብ ተጋርተው ወጠዋል
በሽረ በኩል 4-5-1 አሰላለፍ ሲኖራቸው እንግዳዎቹ ለገጣፎዎቹ ደሞ 4-4-2 አሰላለፍ መግባት ችለዋል፡፡
የመጀመርያ 45 ደቂቃ ሁለቱም ቡድኖች ተመጣጣኝና በሽሬዎች አልፎ አልፎ ወደ ግብ የመድረስ ሁኔታ ቢታይም ግብ ለማግባት 29 ደቂቃ መጠበቅ ግድ ብላቸዋል በ 29 ኛ ደቂቃ ልደቱ ሽሬዎች ቀዳሚ ያደረገች ግብ አስቆጥሮ የግብዋ ባለቤት ልደቱ ጎልዋን አስቆጥሮ በቀድሞ ክለቡ ላይ በማግባቱ ብዙም ደስታውን ሳይገልፅ በደስታ ፋንታ ሲያነባ ነው የታየው ከዚች ግብ በኃላ ለገጣፎዎች ተጭነው የተጫወቱ ቢሆንም ግብ ማስቆጠር ሳይችሉ ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል፡፡
ከእረፍት መልስ ለገጣፎዎች ሃይል የተቀላቀለበት አጨዋወት በመምረጥ ቶሎ ቶሎ ወደ ሽሬ ግብ የደረሱ ሲሆን በግምት ከ 20 ሜትር ያገኙት አወዛጋቢ ቅጣት ምት በ58 ኛ ደቂቃ ዳዊት ቀለምወርቅ በመምታት ወደ ግብነት ቀይሮ ለገጣፎዎች ነጥብ ተጋርተው እንዲወጡ አድርጋ ከዚች ግብ መቆጠር በኃላ የለገጣፎ አስናቀ ተስፋዬ በ2 ቢጫ ካርድ ከሜዳ ሊሰናበት ችሏል፡፡በለገጣፎዎች በኩል ሰአት የመባከን አዝማምያ ቢታይም ውጤቱ ሳይቀየር 90ደቂቃ ተጠናቆ 5ደቂቃ ያክል የባከነ ሰዓት 4ኛ ዳኛ ሳያሳዩ ሌላ ተጨማሪ 7 ደቂቃ ጭማሪ በማሳየት 3ያክል ደቂቃዎች ከተጫወቱ በኃላ የመሀል ደኛው የጨዋታው መጠናቀቂያ ፊሽካ በማሰማት መጠናቀቁን ማወጃቸውን ተከትሎ የሰጡ ሲሆን ሰአት ጭማሪ ሳያሳይ ከደጋፊውና ከሽሬ አመራሮች ዳኛው ላይ ተቃውሞ አሰምተዋል::
- ማሰታውቂያ -
ጨዋታው መጠናቀቁን ተከትሎ የለገጣፎ ከተማ ተጫዋቾች በ ሽሬ ደጋፊዎች በጨብጨባ ታጅበው ከስታድየሙ መውጣት ሲችሉ የእለቱ ዳኞችነና ኮምሽነሩ ከሜዳዎ በፀጥታ ሃይሎች ታጅበው ሊወጡ ችለዋል፡፡
የአሰልጣኞች አስተያየት
ዳንኤል ፀሃየ- ሽረ እንዳስላሴ
“ውጤቱ ለኛ ይገባን ነበር ፡፡ ከእረፍት በፊት እኛ በልጠን ነበር:: ከእረፍት በኃላ ዳኛ በፈጠረብን ተፅእኖ ልጆቻችን ተደናግጠውና ተረብሸው ሊረጋጉ አልቻሉም፡፡ የሃይል አጨዋወት ስለፈቀዱ ልጆቻችን አልተረጋጉም እንጂ ደግመን አግብተን አሸንፈን እንወጣ ነበር፡፡ ሁለት የተሰጠብን ቅጣት ምት አግባብ አልነበረም፡፡ ዳኛ በፈጠረው ስህተት ነጥብ ተጋርተናል ደጋፊው እንደዚ በደል ዶርሰበትም በስርአት ነው ከሜዳ ለቆ እሚወጣው ደስ ሚል ደጋፊ ነው፡፡”
ያሬድ ቶሌራ -ለገጣፎ ከተማ
“ከእረፍት በፊት ሽሬዎች ጥሩ ነበሩ ከእረፍት በፊት የገባብን ግብ ለመቀልበስ ስህተታችን አርመን በመግባት በሁለተኛው አጋማሽ የሽሬዎቹ ደካማና ጠንካራ ጎን ለይተን በመግባት ያሰብነው አሳክተናል፡፡
የተሰጠብን ቀይካርድ አግባብ አደለም የተጨመረው 7ደቂቃም ፍትሃዊ አይደለም 7ደቂቃ እሚያስጨምርም ሰዓት አልባከነም፡፡ ደጋፊው ደስ ይላል ኳስ ለተጫወተ ይደግፋል በስርአት ደስ በሚል ሁኔታ ከሜዳ ወጥተናል፡፡”