13ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች በተደረጉ ጨዋታዎች ቀጥሎ ተካሂዷል።
አዲስ አበባ ላይ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከቅዱስ ጊዮርጊስ 9 ሰዓት ላይ አድርገዋል። ጨዋታው ከዕረፍት መልስ በተቆጠረ ጎል በቅዱስ ጊዮርጊስ አሸናፊነት ተጠናቋል።
ጅማ ላይ ወልድያ ከተማን ያስተናገደው ጅማ አባ ቡና በሜዳው ሽንፈት አስተናግዷል።
- ማሰታውቂያ -
በጨዋታው ወልድያ ከተማ ከእረፍት መልስ ባስቆጠራቸው ሁለት ጎሎች ከሜዳው ውጭ ማሸነፍ ችሏል። ሃዋሳ ላይ በሃዋሳ ከተማና በድሬዳዋ ከተማ መካከል የተደረገው ጨዋታ ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት ተጠናቋል።
አርባ ምንጭ ላይ ሲዳማ ቡናን ያስተናገደው አርባ ምንጭ ከተማ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
ሲጠበቅ የነበረውና 11 ከ30 ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም የተደረገው የደደቢት እና አዳማ ከተማ ጨዋታ ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት ተጠናቋል።
ውጤቱን ተከትሎም ሊጉን ኢትዮ ኤሌክትሪክን ያሸነፈው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአዳማ ከተማ እኩል 25 ነጥብ በመያዝ በግብ ክፍያ መምራት ጀምሯል።
ደደቢት ደግሞ በ24 ነጥቦች ሶስተኛ ደረጃ ን ይዟል።
የደረጃ ሰንጠረዥና የከፍተኛ ጎል አስቆጣሪዎችን ደረጃ ይመልከቱ
# | ክለብ | ተጫ | ልዩ | ነጥብ |
---|---|---|---|---|
1 | ቅዱስ ጊዮርጊስ | 13 | 13 | 25 |
2 | አዳማ ከተማ | 13 | 5 | 25 |
3 | ደደቢት | 13 | 8 | 24 |
4 | ሲዳማ ቡና | 13 | 0 | 21 |
5 | ፋሲል ከተማ | 12 | 5 | 20 |
6 | አርባምንጭ ከተማ | 13 | 3 | 20 |
7 | ኢትዮጵያ ቡና | 13 | 0 | 20 |
8 | መከላከያ | 13 | -1 | 18 |
9 | ወልድያ | 13 | 0 | 17 |
10 | ወላይታ ድቻ | 12 | 0 | 16 |
11 | ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ | 12 | -1 | 13 |
12 | ድሬዳዋ ከተማ | 13 | -6 | 12 |
13 | ኢትዮ ኤሌክትሪክ | 13 | -4 | 11 |
14 | ጅማ አባ ቡና | 13 | -7 | 10 |
15 | ሀዋሳ ከተማ | 12 | -7 | 8 |
16 | አዲስ አበባ ከተማ | 11 | -8 | 8 |