17ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ የሳምንቱን ተጠባቂ አንድ ጨዋታን አስተናግዷል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም ከቀኑ 10 ሰዓት የተደረገው ጨዋታ የሊጉን መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከተከታዩ ደደቢት አገናኝቷል።
በጨዋታው ቅዱስ ጊዮርጊስ መሪነቱን ማጠናከር የሚችልበትን ድል አስመዝገቧል።ፈረሰኞቹ ጨዋታውን 3 ለ 2 ሲያሸንፉ፥
ሳልሃዲን ሰዒድ በ 15ኛ እና በ50ኛ በመጀመሪያው አጋማሽ እና በሁተኛው አጋማሽ 2 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።
- ማሰታውቂያ -
ምንተስኖት አዳነ ቀሪዋን ጎል በ31ኛ ደቂቃ ላይ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሲያስቆጥር፥ ለደደቢት ጌታነህ
ከበደ በ71ኛ ደቂቃ እና አበባው ቡጣቆ በ73ኛ ደቂቃ ላይ ከቅዱስ ጊዮርጊስ በራሱ ግብ ላይ አስቆጥረዋል።
ውጤቱን ተከትሎም ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊጉን በ35 ነጥብ መምራት ጀምሯል።
ተሸናፊው ደደቢት እና ሲዳማ ቡና ደግሞ በእኩል 28 ነጥቦች በጎል ክፍያ ተበላልጠው ይከተሉታል። ሌሎች ጨዋታዎች ነገ ሲካሄዱ፥ 9 ሰዓት
በአዲስ አበባ ስታዲየም ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከድሬዳዋ ከተማ ይገናኛሉ። ሃዋሳ ላይ ሃዋሳ ከተማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ወልድያ ላይ ወልድያ ከተማ ከአርባ ምንጭ ሲጫወቱ ይርጋለም ላይ ደግሞ ሲዳማ ቡና ከአዳማ ከተማ ይገናኛሉ። ወላይታ ዲቻ በሶዶ ፋሲል ከተማን ሲያስተናግድ ጅማ ላይ ደግሞ ጅማ አባ ቡና ከአዲስ አበባ ከተማ ይጫወታሉ።
በአዲስ አበባ ስታዲየም ደግሞ 11 ሰዓት ከ30 ኢትዮጵያ ቡና ከመከላከያ የሳምንቱን የመጨረሻ የሊጉን መርሃ ግብር ያከናውናሉ።
የደረጃ ሰንጠረዥ እና ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪዎችን ይመልከቱ
# | ክለብ | ተጫ | ልዩ | ነጥብ |
---|---|---|---|---|
1 | ቅዱስ ጊዮርጊስ | 17 | 20 | 35 |
2 | ደደቢት | 17 | 8 | 28 |
3 | ሲዳማ ቡና | 16 | 4 | 28 |
4 | አዳማ ከተማ | 16 | 4 | 27 |
5 | ፋሲል ከተማ | 16 | 5 | 26 |
6 | ኢትዮጵያ ቡና | 16 | 3 | 25 |
7 | አርባምንጭ ከተማ | 16 | 1 | 22 |
8 | መከላከያ | 16 | -1 | 21 |
9 | ወልዲያ ከተማ |
16 | 0 | 20 |
10 | ወላይታ ድቻ | 16 | -5 | 18 |
11 | ሀዋሳ ከተማ | 16 | -5 | 17 |
12 | ኢትዮ ኤሌክትሪክ | 16 | -2 | 16 |
13 | ድሬዳዋ ከተማ | 16 | -8 | 16 |
14 | ጅማ አባቡና | 16 | -5 | 14 |
15 | ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ | 16 | -9 | 14 |
16 | አዲስ አበባ ከተማ | 16 | -9 | 10 |
ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪዎች