ባለ ከለሯና ሳምንታዊዋ ተወዳጇ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ እንደተለመደው ሁሉ በነገ የማክሰኞ እትሟም የሚወዱትን ሀገራዊና የባህር ማዶ ጣፋጭ ዘገባዎችን ይዛላችሁ ትቀርባለች፤ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በነገው የሀገር ውስጥ የስፖርት ዘገባዋ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን አስመልክቶ በ8ኛው ሳምንት ከተደረጉት ጨዋታዎች መካከል ድል የቀናቸው የኢትዮጵያ ቡናና የደደቢት ቡድኖችን አስመልክቶ ከቡድኑ ተጨዋቾች ውስጥ የኢትዮጵያ ቡናውን አማካይ ኤልያስ ማሞና የደደቢቱን አጥቂ ጌታነህ ከበደን በቡድናቸውና በራሳቸው አቋም ዙሪያ ጠይቀናቸው ምላሽን የሰጡበት ከእዚያ ውጪም ሌሎች የሀገር ውስጥ መረጃዎችንም በማቅረብ እናንተ ውድ አምባቢዎቻችን እንድታነቡት ጋብዞዎታለች፤ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በየሳምንቱ ይዛው በምትቀርበው የOLDIES BUT GOODIES አምዷም የነገው እትሟ እንግዳዋ አድርጋ ያቀረበችው ለኦሜድላ ክለብ ለ18 ዓመታት ተጫውቶ ያሳለፈውን የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አመለሸጋ ተጨዋች ተስፋዬ ፈጠነን ሲሆን እሱም ባሳለፈው የተጨዋችነት ሕይወቱና ስለግል ህይወቱም ጠይቀነው ምላሹን በአማረ ሁኔታ ሊሰጥ ችሏል፤ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በባህር ማዶ ዘገባዋ በነገው እትም ይዛሎት የምትቀርበው በኤልክላሲኮው የሪያል ማድሪድና የባርሴሎና ጨዋታ ዙሪያ ከጨዋታው በኋላ ምን ተባለ በሚለው ጉዳይ ላይ በሜሲ በሱዋሬዝና በዚዳን ዙሪያ ያልተሰሙ አስገራሚ ዜናዎችን ልታስነብቦትም ተዘጋጅታለች፤ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግን አስመልክቶም በማንቸስተር ሲቲ፣ በአርሰናል በማንቸስተር ዩናይትድና በሊቨርፑል ክለብ ዙሪያም ከጨዋታው በኋላ ያልተሰሙ አዳዲስ ዘገባዎችንም ይዛለች፤ ሀትሪክ ስፖርት ከእነዚህ ውጪ እንደተለመደው በመዝናኛ ዓምዷም የሚወዱትን ምርጥ ምርጥና ጣፋጭ ዜናዎችንም ለእናንተ በማቅረብም መሰናዶዋን አጠናቃለች፤ እንዳታመልጦት፡፡
በሳምንት አንድ ቀን በገበያ ላይ የምትውለው ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በአጭር ቀናት ውስጥ በሳምንት ሁለት ቀንም ለመውጣት የመጨረሻው ዝግጅት ላይ ትገኛለች፤ በእዚህ አዲስ እትሟም ለየት ባለ መልኩ አዳዲስ አምድን ከፍታና በልዩ መሰናዶ ከእናንተ ጋር ልትገናኝም ዝግጁ ሆናለች፤ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣን በድረ-ገፅም hatricksport.com በሚለው ላይ የምታገኟት ይሆናል፡፡
የሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የነገው እትም የፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡
- ማሰታውቂያ -