በዘንድሮ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ሲወዳደር የነበርው መቐለ ከተማ ምርጥ ብቃቱን በማሰየት ቡድኑ ወደ ፕሪሜየር ሊጉ እንዲያድጉ ጉልህ ሚና ከተጫወቱ ተጫዋቾች ውስጥ የፊት መስመሩ አጥቂ አማኑኤል ገ/ሚካኤል ግንባር ቀደሙ ነው፡፡
ተጨዋቾች ከመከላከያ እና ከፋሲል ከተማ ጋር ስሙ ሲነሳ ቢቆይም በመጨረሻም ለክለቡ በ2.4 ሚሊዮን ብር ለሁለት ዓመት እሚያቆየውን የፊርማ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡
እንዲሁም መቐለ ከተማ 10ተጫዋቾችን ፊርማ ሲያድስ የቀደሞ የክለቡ በረኛ የነበረው በአሁን ሰዓት በወሎ ኮምቦልቻ እሚገኘውን ሙሴ መጠኑ ባለታወቀ የፊርማ ስምምነት ክለቡን ተቀላቅሏል ፡፡