የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ 5ኛ ሳምንት ጨዋታ የሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ግርጌ ላይ እሚገኘው አርባምንጭ ከተማ መከላከያን 2-0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል::
የመጀመሪያው የጨዋታ አጋማሽ እንደተጀመረ በተደጋጋሚ ወደ ጎል መድረስ የቻሉት መከላከያ ሲሆኑ በ ሲሳይ ባንጫ ብቃት ጎል ማስቆገር አልቻሉም ነበር፡፡
በ20ኛ ደቂቃ ላይላኪ ሰኒ የሞከራት ኳስ ከጨዋታ ወጪ አቋቋም ላይ በመሆኑ ከጨዋታ ውጪ ልትሆን ችላለች፡፡
በመከላከያ በኩል በተደጋጋሚ ወደ ጎልመድረስ ቢችሉም የአርባምንጭ ግብ ጠባቂን አልፈው ጎል ማስቆጠር አልቻሉም ነበር፡፡
ወጣቱ የአርባምንጭ ከተማ ተጫዋቾችብርሀኑ አዳሙ አማካኝነት ወደ መከላከያ ግብ ክልል በተደጋጋሚ ለመድረስ ቢችሉም ጎል ማስቆጠር አልቻሉም ነበር፡፡ የመጀመሪያው አጋማሽ 0-0 በሆነ ውጤት ሊጠናቀቅ ችሏል፡፡
በሁለተኛው ግማሽ በአርባምንጭ ከተማ አማካኝነት ኳስ ሲጀመር ከተጨዋች ለውጥ ጋር ነበር የጀመሩት ታድዮስ ወልዴን በአለልኝ አዘነ ቀይረው ሲያስገቡ የመጀመሪያ የጎል ሙከራቸውን በላኪ ሳኒ አማከኝነት ማድርግ ችለውም ነበር፡፡
60ኛ ደቂቃ ላይ አርባምንጭ ከተማው ፀጋዬ አበራ አመቻችቶ ያቀበለውን ኳስ ወጣቱ አጥቂ ብርሀኑ አዳሙ በሚገባ ተጠቅሞ ቡድኑን መሪ አድርግዋል፡፡
ከጎልዋ መቆጠር በኃላ መነቃቃት ውስጥ የገቡት አዞዎቹ ተጭነው ለመጫወት ችለዋል፡፡ቀይረው ባስገቡት ወጣቱ ተስፈኛ አለልኝ አዘነ አማካኝነት ሁለተኛ የሞከሯት ኳስ የጎል ብረት ልትመልስበት ችላለች፡፡
- ማሰታውቂያ -
በእለቱ በጥሩ ሁኔታ ሲንቀሳቀስ የነበረው ብርሀኑ አዳሙ በተመልካቾች ዘንድ አድናቆትን መግኘት ችሏል፡፡
ጨዋታው ሊጠናቀቅ የደኛ ፊሺካ በሚጠበቅበት ሰዓት ፀጋዬ አበራ ግሩም የሆነ ኳስ አስቆጥሮ የአስልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም የአሰልጣኝነት ቆይታ ለግዜው ሊያራዝመው ችሏል፡፡ጨዋታውም በአርባምንጭ ከተማ 2-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡