በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ በእልህ
አስጨራሹና በፈታኙ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር
ከአንድም ሶስት ጊዜ ቡድኖችን ወደ ላይ
በማሳደጉ “The Promotion Expert” የሚል
ቅፅል ስምን ለማግኘት የቻለው፡፡
የኢትዮጵያ
ውሃ ስፖርትን፣ ዳሽን ቢራን እና አሁን
ደግሞ የጅማ ከነማን ቡድንን ከፍተኛ ሊጉ
ወደ ፕሪሜየር ሊጉ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ
ሶስት ቡድኖችን ወደ ላይ በማውጣት ሀትሪክ
ሰርቷል፡፡ የጅማ ከተማ ቡድን በእግር ኳስ
ታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገሪቱ ታላቁ ሊግ
በመቀላቀልና የእልህ አስጨራሹና ፈታኙን
የከፍተኛ ሊግ አጠቃላይ ሻምፒዮን በማድረግ
በታሪክ ላይ ታሪክ ያፃፈው አሰልጣኝ መኮንን ገ/ዮሃንስ ጅማ ከተማ በይፋ አሰናብቷል፡፡
በምትካቸውም ጅማ አባቡና ከመውረድ ያላዳኑትን የቀድሞውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ፤ ኢትዮጵያ መድን ፤ ትራንስ ኢትዮጵያ ፤ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፤ኢትዮጵያ ቡና ፤ ደደቢት ፤ መከላከያን ማሰልጠን የቻሉትን አሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌን በይፋ የአንድ አመት ኮንትራት አስፈርሟዋል፡፡