ኢትዮጵያ ቡና አስልጣኝ ድራጋን ፓፓዲችን ለሁለተኛ ግዜ ወደ ኢትዮጵያ ቡና በመምጣት የክረምቱን ወራት የቅድመ የውድድር ዝግጀት ግዜ ክለቡን በማዘጋጀት እንዳሳለፉ ይታወቃል።
የ78 ዓመቱ ፓፓዲች ደንገት ባጋጠማቸው የጤና እክል ወደ ሆስፒታል በመግባት ህክምና መከታተል ከጀመሩ ቀናቶች ተቆጥረዋል ።
ህክምናውን እየተከታተሉበት ካለው ሃሌ ሉያ ሆስፒታል ዶክተሮች እየተሰማ ያለው ዜና በዚህ ሰዓት ለቡና ደጋፊዎች አስደንጋጭ ሊሆን ይችላል።
ዶክተሮቹ ለናይጄሪያው ፓፓዲች ወኪል እደተናገሩት ጉዳዩ አሳሳቢ የልብ ህመም ስለሆን ዳግም ወደ እግር ኳስ አሰልጣኝነት መመለስ እንደሌለበት ፤ ከእድሜ ጋር ተያይዞ ጭንቀት እና ደስታ አስልጣኙን ወደ ከፋ አደጋ ሊመራው ስለሚችል ወደ ሀገሩ ተመልሶ የተሻለ ህክምና እና እረፍት እንዲያደርግ ሞያዊ ምክር ለግሰዋል።
የኢትዮጵያ ቡና አመራሮች የዶክተሮቹን ውሳኔ ከሰሙ በሀላ ከፓፓዲች ጋር የመለያየታቸው ነገር እርግጥ በመሆኑ አማራጮችን መፈለግ ጀምረዋል።
አሁንም ከሰርቢያ ሌላ አሰልጣኝ ለማምጣት እየሞከረ መሆኑ ተሰምቷል፡፡