በመሸሻ ወልዴ /G.boys/
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ለሐዋሳ ከተማ ለሲዳማ ቡናና ለኤሌክትሪክ ክለቦች ተጫውቶ ያሳለፈው ብሩክ አየለ የፕሪሚየር ሊግ አዲስ ተቀላቃይ ለሆነው የወልዋሎ አዲግራት ዮኒቨርስቲ ክለብ ለአንድ ዓመት ፊርማውን ሊያኖር ችሏል፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ በኳስ አጠቃቀማቸው ጥሩ እንቅስቃሴ ከሚያደርጉ ተጨዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ብሩክ የወልዋሎ ክለብን ለተቀላቀለበት የአንድ ዓመት ቆይታውም 1.2 ሚሊየን ብር የፊርማ ክፍያ እንደተፈፀመለትም መረጃዎች እየጠቆሙ ይገኛል፡፡
የሐዋሳ ከተማና የሲዳማ ቡና ተጨዋች በነበረበት ወቅት በአሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ምርጥ የእግር ኳስ ተጨዋችነት ጊዜን ያሳለፈው ብሩክ በኤሌክትሪክ ተጨዋችነቱ ዘንድሮ የተረጋጋ ጊዜን ባያሳልፍም ተጨዋቹ ካለው ጥሩ ብቃት አኳያ የአሰልጣኝ ብርሃኔ ገብረ እግዚአብሄርን ክለብ ወልዋሎን ይጠቅማል ተብሎ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቶታል፡፡