የአፍሪካ እግር ኳስ ማህበር (CAF) ኘሬዚዳንት ሚ/ር አማድ አማድ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ሐምሌ 30 ቀን 2009 ዓ.ም ምሽት አዲስ አበባ ይገባሉ፡፡
ከካፍ ኘሬዚዳንት ጋር እሁድ ምሽት 3፡00 ሰዓት አዲስ አበባ እንደሚገቡ የሚጠበቁት የካፍ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ሚ/ር ሱሌይማን ሀሰን ዋበሪ እና ሁለት የቅርብ ረዳቶቻቸው ናቸው፡፡
ኘሬዝዳንቱ በአዲስ አበባ በሚያደርጉት የሦስት ቀናት ቆይታቸው ከክቡር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ከክቡር የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ኘሬዚዳንት እና ከሌሎች ከፍተኛ የስፖርት መሪዎች ጋር በእግር ኳስ ልማትና በቀጣይነት በትብብር በሚከናወኑ ሁሉን አቀፍ ክንውኖች ዙሪያ እንደሚመክሩ ይጠበቃል፡፡